09
Apr
ከ24 ዓመት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማሳለጥ የተቋቋመው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጥምረት በየጊዜው አዳዲስ አባላትን በመሳብ ላይ ይገኛል። ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከአንድ ዓመት በፊት ይህን ጥምረት ለመቀላቀል በይፋ ከጠየቀች በኋላ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ጀምሮ አባል መሆኗ ይታወሳል፡፡ ጥምረቱም የመቋዲሾን ጥያቄ ለመመለስ ባለሙያዎቹን አሰማርቶ የተለያዩ ግምገማዎችን ሲያደርግ ቆይቶ ሶማሊያን ስምንተኛዋ አባል ሀገር አድርጎ መቀበሉን በወቅቱ አስታውቋል። ዋና መቀመጫውን አሩሻ ታንዛኒያ ያደረገው ይህ የኢኮኖሚ ጥምረት በቀጣይ በሚያደርገው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን በይፋ በአባልነት እንደሚቀበል ይጠበቃል። ዋና ጸሀፊው አክለውም “የጥምረቱ ቀጣይ አባል ሀገር ኢትዮጵያ ልትሆን ትችላለች፣ ኢትዮጵያ አባል የመሆን ፍላጎትም አሳይታለች” ሲሉ ተናግረውም ነበር፡፡ የህብረቱ ዋና ፀሐፊ የሆኑት ፔኒና ማንሎንዛ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ…