12
Apr
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ የክልል ልዩ ሀይሎችን በሚመለከት በተፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። ተቋሙ እንዳለው የልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀትን ውሳኔ ትግበራ በውይይትና የሰዎችን ሰብአዊ መብቶች አደጋ ላይ በማይጥል ሁኔታ ሊከውን ይገባል ሲል አሳስቧል ኢሰመኮ መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራልና በክልል መደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ መልሶ ለማደራጀት ያሳለፈውን ውሳኔና ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ የጸጥታ መደፍረስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን በተመለከተ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ በተለይም በቆቦ፣ በባሕር ዳር፣ በወረታ፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረ ብርሃን እና በመራዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ መንገድ መዘጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥጫዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች…