መነሻ ገፅ

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር መፈቱን የአለም ባንክ ገለጸ

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር መፈቱን የአለም ባንክ ገለጸ

የዓለም ባንክ ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ በቅርቡ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በሚደረገው ውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ የመጫወቻ ሜዳ እንደገጠመውና ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረገ ይፋ አድርጓል። "የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ግምገማ" በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ሪፖርት፣ በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል ያለውን ያልተመጣጠነ ውድድር በዝርዝር ይተነትናል። ሪፖርቱ እንደሚለው፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ሳፋሪኮም 850 ሚሊዮን ዶላር የፈቃድ ክፍያ ባለመክፈሉና በስድስት የገበያ ዘርፎች ላይ የበላይነት ያለው ተቋም (SMP) ሆኖ በመቆጠሩ ውድድሩ ፍትሃዊ አይደለም። ኢትዮ ቴሌኮም ከደንብ አስከባሪው ከተቀመጠው የመገናኛ ዋጋ (MTR) በታች የድምጽ ጥሪ ዋጋ በማቅረቡ፣ ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚደረግ እያንዳንዱ ጥሪ ላይ ኪሳራ እንደሚያስተናግድ ሪፖርቱ ገልጿል (በወር 1.6 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል)።…
Read More
በኢትዮጵያ የኢንተርፕርነርሺፕ ባንክ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የኢንተርፕርነርሺፕ ባንክ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በፋይናንስ ለመደገፍ 'ኢንተርፕርነርሺፕ ኢንቨስትመንት ባንክ' ሊቋቋም መሆኑ ተገልጿል። ባንኩ በ20 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል የሚመሰረት ሲሆን፣ ወጣቶች ለድጋፍ የሚያስይዙት ዋስትና የፈጠራ ሀሳባቸውን ብቻ እንደሚሆን ተጠቁሟል። ባንኩን ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ ፊርማ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ተቋሙ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለኢንተርፕራይዞች አቅም መጎልበት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል። ይህ እርምጃ መንግስት የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያወጣቸውን ፖሊሲዎች ወደ ተግባር የመቀየር አካል መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ገልጸው፣ ባንኩ የወጣቶችን ጥያቄ በመመለስ የፈጠራ አቅማቸውን ለማጎልበት ያስችላል ብለዋል። ከመነሻ ካፒታሉ 10 ሚሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ በድጋፍ…
Read More
ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ለማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ተባለ

ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ለማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ተባለ

‎መደበኛ ባልሆነ እና በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሚፈልሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ሲሉ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሕገ-ወጥ ፍልሰተኞቹ ከሚያጋጥሟቸው የከፉ ችግሮች መካከል፤ እሥር፣ የወሲብ ባርነት፣ መደፈር፣ ከባድ አካላዊ ቅጣት፣ አካል ጉዳተኝነት፣ እንደ ኩላሊት ያሉ የውስጥ አካልን በግዳጅ መዘረፍ እንደሚገኙበት ገልጸዋል። ይሁንና ሚንስትሯ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ለየትኛው ሀገር በውትድርና እንደተመለመሉ አልጠቀሱም። ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡት ዜጎች ከአካል ጉዳት እና የግዳጅ ውትድርና በተጨማሪ፤ ለአዕምሮ ጤና እክል እና ለሥነ-ልቦና ቀውስ ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተነስቷል። ሚኒስትር ደኤታዋ አያይዘውም፤ የሰው ልጅ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለማጣጣም ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱ ግድ ቢሆንም፤ እንቅስቃሴው ሕጋዊ መስመርን…
Read More
ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ሀገሪቱ ከሬሚታንስ ገቢ 35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት አቅም እንዳላት ተገልጿል ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ከሚላክላት ገንዘብ (ሬሚታንስ) የምታገኘው ገቢ የሀገሪቱን አቅም 22 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ሳውዲ አረቢያ ከተሞች ከኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር የተወያዩት ፕሬዝዳንቱ አሁን ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከሬሚታንስ ገቢ እየተገኘች ያለው ገቢ 7.2 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነዉ ብለዋል። አቶ አቤ ሳኖ እንዳስረዱት፣ አሁን ካለው የገንዘብ ፍሰት ቀሪው 78 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር…
Read More
ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር የሚያመርተው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል ብለዋል። በተመሳሳይ በዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን የነዳጅ ማጣሪያ ስራ ማስጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡ ማጣሪያው ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ…
Read More
በሶማሊ ክልል ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ተጀመረ

በሶማሊ ክልል ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ተጀመረ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የዩሪያ ማዳበሪያ እና ጌዴ ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን አስጀምረዋል። የዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ይገነባል ተብሏል። ጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ ደግሞ የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል። የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለውም ተብሏል። በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል። ከአንድ ወር በፊት አሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ…
Read More
አቢሲንያ ባንክ ሰባት ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ

አቢሲንያ ባንክ ሰባት ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ

አቢሲንያ ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ ከ286 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታውቋል። አቢሲንያ ባንክ በዛሬው ዕለት ዓመታዊ የባለአክስዮኖች 29ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው አካሂዷል። በጉባኤው ላይ እ.ኤ.አ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 286 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት አጠቃላይ ሀብት ማለትም ከ222 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር የ63 ነጥብ 9 ቢሊዮን ወይም የ28 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን የአቢሲኒያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መኮንን ማንያዘዋል ገልጸዋል። ባለፈው የሒሳብ ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢው 39 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ ውጤቱ ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 ነጥብ 3 ቢሊዮን…
Read More
ኢትዮጵያ በ1 ቢሊዮን ዩሮቦንድ ዕዳ ዙሪያ አዲስ ውይይት ጀመረች

ኢትዮጵያ በ1 ቢሊዮን ዩሮቦንድ ዕዳ ዙሪያ አዲስ ውይይት ጀመረች

ኢትዮጵያ የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ዕዳዋን እንደገና ለማዋቀር ከግል ባለቤቶች ጋር ሚስጥራዊ ውይይት ጀምራለች። የኢትዮጵያ መንግስት የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮቦንድ ዕዳን እንደገና ለማዋቀር (restructure) ከዓለም አቀፍ የቦንድ ባለቤቶች ኮሚቴ ጋር ይፋዊ እና ሚስጥራዊነትን ያካተተ ውይይት መጀመሩን ብሉምበርግ ዘግቧል። ይህ እርምጃ ሀገሪቱ በከባድ የዕዳ ጫናዋን ለማቃለል በምታደርገው ጥረት ውስጥ እንደ ወሳኝ ምዕራፍ ተወስዷል። ውይይቱ "restricted" ተብሎ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ማለት በድርድሩ ላይ የሚሳተፉት አበዳሪዎች (የቦንዱ ባለቤቶች) "የምስጢራዊነት ስምምነት" (NDA) መፈረም ነበረባቸው። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስት ለስምምነቱ መሳካት ወሳኝ የሆኑ ሚስጥራዊ የኢኮኖሚ መረጃዎችን ለአበዳሪዎቹ እንዲያካፍል ያስችለዋል። ስምምነቱን የፈረሙ ባለቤቶች በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያን ቦንድ መሸጥም ሆነ መግዛት አይችሉም። ይህ የውይይት እርምጃ የመጣው ኢትዮጵያ…
Read More
የባንኮች ብድር ዕድገት ጣሪያ ወደ 24 በመቶ አደገ

የባንኮች ብድር ዕድገት ጣሪያ ወደ 24 በመቶ አደገ

ብሔራዊ ባንክ አሁን ያለውን የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ ለማስቀጠል እና የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነት ለመጠበቅ በመስከረም ወር ላይ ሊነሣ ይችላል ተብሎ የተገመተዉ የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያን ሙሉ ለሙሉ ከማንሳት ይልቅ ገደቡ ለጊዜው ከ18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡ የባንኮች የብድር ዕድገት ገደብ መነሣት የብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ አቋም ለማመልከትና የገንዘብ ፖሊሲ መዋቅሩን የተሻለ ለማድረግ እንደሚረዳ ይታመናል ሲል ኮሚቴው አስረድቷል፡፡ ኮሚቴው  በጉዳዩ ላይ በወደፊት ስብሰባዎቹ ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ አንደሚያቀርብም ጠቅሷል፡፡ የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይም ወስኗል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ለሚሰጣቸው የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት እና የብድር አገልግሎት የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ፤ እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት…
Read More
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ62 ዓመታት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ታሪካዊ የሚባል ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋትም የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑም ተገልጿል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ፈርመዋል። ስምምነቱ ከሃገራቱ በተጨማሪ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት የጎላ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ተናግረዋል። በቀጣይም ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ የኬንያ መከላከያ በቁርጠኝነት ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ መናገራቸውንም ከኢኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ኢትዮጵያና…
Read More