youthfestival

ከ10 ሺህ በላይ የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ተዘጋጀ

ከ10 ሺህ በላይ የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ተዘጋጀ

(ኢትዮ ነጋሪ፣ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ) “ዛሬን በንቃት፣ ነገን በስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ይህ ሃገር-አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ከሚያዚያ 21 እሰከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተበሏል፡፡ ፌስቲቫሉ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅተ የገንዘብ ድጋፍ በሚተገበረው ከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም በኩል የሚዘጋጅ ሲሆን አምሬፍ ሄልዝ አፍሪካ ከአጋሮቹ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ፌስቲቫሉን እንደሚመራ ተገልጿል፡፡ የከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ፓርቲ አቶ ቻላቸው ጥሩነህ እንዳሉት ወጣቶችን በተለያዩ መስኮች ብቁ ማድረግ የዚህ ፌስቲቫል ዋና አላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፌስቲቫሉ የወጣቶች ስኬት ዕውቅና የሚሰጥበት፣ ከተለያዩ ዘርፎች የመጡ ወጣቶች ልምድ የሚለዋወጡበት፣ እንዲሁም ለበለጠ ስኬት…
Read More