30
Mar
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ዛሬ ጠዋት በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል። ኃላፊው ወደ ስራ ለመሄድ ከቤታቸው በወጡበት ጊዜ በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተገደሉም ነው የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት በማህበራዊ ገጽ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው። አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊነትን ጨም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ሲያገለግሉ መቆየታቸውም ተገልጿል። የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ…