18
Aug
የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ከአንድ ሳምንት በኋላ በላቲን አሜሪካዋ ፔሩ አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ተመርጠው የመጨረሻ ልምምድ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለውድድሩ ከመረጣቸው አትሌቶች መካከል የ17 አመቱ አትሌት ሰው መሆን ታሪኩ አንዱ ነው፡፡ ይህ አትሌት ባሳለፍነው እሁድ ነሀሴ 5 ቀን 2016 ዓም የከሰዓት በኋላ ልምምድ ለመስራት ወደ ጫካ ወጣ ብሎ ልምምዱን ጨርሶ እያቀዘቀዘ ባለበት ያልታሰበ ሰው ጥቃት አድርሶበታል ተብሏል፡፡ አትሌቱን አንድ ሰው ከቀረበው በኋላ ፓሊስ ነኝ በማለት ራሱን ካስተዋወቀው በኋላ እዚህ አካባቢ ቁማር የሚጫወቱ ታውቃለህ በማለት ሲጠይቀው አላውቅም ብሎ እንደመለሰ ነገር ግን ወዲያው በፎጥነት ይህ ሰው አንገቱን ሲይዘው አትሌቱም…