Ethiopia

የጉምሩክ ቀረጥ ገቢ ባለፉት 7 ዓመታት በግማሽ መቀነሱ ተነገረ

የጉምሩክ ቀረጥ ገቢ ባለፉት 7 ዓመታት በግማሽ መቀነሱ ተነገረ

ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ የጉምሩክ ቀረጥና ተጨማሪ ቀረጥ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር በግማሽ መቀነሱ ተገለጸ። ይህ ቅናሽ በዋናነት ከውጭ የሚገቡ የሸቀጦች መጠን እና ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት እንደሆነ ተጠቁሟል። እኤአ 2015/16 ጀምሮ የነበረው የጉምሩክ ቀረጥና ተጨማሪ ቀረጥ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 2.1% የነበረ ሲሆን፣ ይህ አሃዝ በ2022/23 ወደ 1.0% ዝቅ ብሏል። የዚህ መቀነስ ዋነኛ ምክንያት፣ ከውጭ የሚገቡ የሸቀጦች መጠን ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ24% ወደ 10% በመውረዱ እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስቴር የሰሞኑን ጥናት ያመለክታል። ይህ የገቢ ቅናሽ አጠቃላይ የግብር እና የሀገር ውስጥ ምርት ጥምርታ መውረድ ውስጥ አንድ አራተኛውን ይዟል። ከ2015/16 እስከ 2021/22 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የውጭ ምርቶች መጠን መቀነስ በዋነኝነት በካፒታል…
Read More
ቻይና ሰራሹ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ተከለከለ

ቻይና ሰራሹ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ተከለከለ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከሲኖትራክ ምርት ተሽከርካሪዎች ጋር ተያይዞ በታየው የጥራትና ቴክኒክ ጉድለት ምክንያት፣ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን አሳውቋል። ይህ ውሳኔ በሰዎች ህይወት ላይ በተደጋጋሚ አደጋ እየደረሰ በመሆኑ እንደተወሰነ ኢትዮ ነጋሪ ለጉምሩክ ኮሚሽን በተጻፈ ከሰርኩላር ደብዳቤ ላይ ተመልክቷል። ሚኒስቴሩ በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል ለጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በሙሉ ባስተላለፈው መረጃ መሰረት፣ የሲኖትራክ ካምፓኒው የጥራት ጉድለቶቹን እስኪያስተካክል ድረስ ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምንም ዓይነት የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ማስገቢያ ፍቃድ እንደማይሰጥ አስታውቋል። ከዚህም ባሻገር፣ ሚኒስቴሩ ፊርማና ማህተም በማስመሰል የሲኖትራክ ማስገቢያ ፍቃድ በማዘጋጀት ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚሞክሩ ሰዎች መኖራቸውን መረጃ እንዳገኘ ገልጿል። ይህን ተከትሎ፣ ከግንቦት 27 ቀን 2017…
Read More
ከአዲስ አበባ-ሀርጌሳ- ጅቡቲ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ሊጀመር ነው

ከአዲስ አበባ-ሀርጌሳ- ጅቡቲ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ሊጀመር ነው

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ወራት ወደ ሶማሊላንድ እና ጅቡቲ የአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት የማስጀመር እቅድ እንዳላት ገልጻለች። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ባረኦ ሀሰን መቀመጫውን ኬኒያ ናይሮቢ ያደረገው አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች ባለቤት እና ማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይተዋል። አቶ በሪኦ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር በተያዘው በጀት አመት ኬኒያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሌላንድ በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት እቅድ መያዙን ገልጸዋል። አገልግሎቱን የመንግስትና ግሉን ዘርፍ ትብብር በማጠናከር በጋራ እንደሚሰራም ሚንስቴር ዴዔታው ተናግረዋል። በመሆኑም እንደሚኒስቴር መስሪያቤት በሁለቱ ሀገራት በትብብር ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ የህግ ማዕቀፎችን የማመቻቸቱን ስራ በትኩረት እንደሚሰራ እና በድርጅቱ በኩል አስፈላጊውን ሂደት አሟልተው እንዲመጡ ከስምምነት መደረሱን ሚንስቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ያወጣው መግለጫ ያስረዳል። የአቢሲኒያ ሌግዠሪ…
Read More
የኢትዮጵያ ሙቀት በየዓመቱ ከአንድ ድግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሙቀት በየዓመቱ ከአንድ ድግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በኢትዮጵያ የሙቀት መጠን በየዓመቱ በአማካይ ከ1 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ ነው ተብሏል ኢትዮጵያ ለአለም ሀገራት የሙቀት መጨመር ያላት የበካይ ጋዝ ልቀት ድርሻ ግን 0.04 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ያደጉት ሀገራት ለአፍሪካ በየጉባኤው ቃል የሚገቡትን የአየር ንብረት ለውጥ መደገፊያ የፋይናንስ ድጋፍ እየሰጡ ስላልሆነ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የሚሰራው ስራ የሚፈለገውን ያህል መሆን አልቻለም ተብሏል፡፡ ይህ የተነገረው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረውና ኢትዮጵያ ከጳጉሜ 3 እስከ 5 ከምታሰናዳው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አስቀድሞ በተሰናዳ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዛሬ ያሰናዳውና ነገም የሚቀጥለው ጉባኤና ኢግዚብሽን ከዋናው ጉባኤ በፊት የሚደረግ ቅድመ ጉባኤ ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ…
Read More
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ፡፡ የፈንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በኢትዮጵያ የወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ ከተሠማራው የኖርዌው አኮቦ የማዕድን ኩባንያ  ሦስት ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 7.4 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ታዬ፤ “በአኮቦ ማዕድን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መስፋፋት ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ እመርታ ነው” ብለዋል፡፡ ውሳኔው ኢትዮጵያ ከክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ የአክስዮን ገበያ እንድትመለስ ያደረገና ለቀጣይ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንቶች በር የከፈተ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢንቨስትመንቱ አኮቦ አዲስ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የሚደግፍ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን ወርሃዊ የወርቅ…
Read More
የመንግስት ሹመኞች የክብር ዶክትሬት ሽልማት እንዳይሰጡ ታገዱ

የመንግስት ሹመኞች የክብር ዶክትሬት ሽልማት እንዳይሰጡ ታገዱ

ትምህርት ሚንስቴር በሀላፊነት ላይ ያለ የመንግስት ሹመኛ ወይም ተመራጭ ለክብር ዶክትሬት እንዳይታጩ የሚከለክል መመሪያ አውጥቷል። መመሪያው 8 ዙር ተማሪዎችን ያላስመረቁ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወይም (PhD) የማያስተምሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተመራው ይህ መመሪያ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡ በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ የክብር ዶክትሬት የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፈርትን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ቢያንስ ከ8 ጊዜ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቁ እና የሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡ በዚህም መሰረት ሰላሌ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቅደላ አምባ፣ ራያ፣…
Read More
ኢትዮጵያ አዲስ የክሪፕቶ ማይኒንግ የኤሌክትሪክ ኃይል ስምምነት እንደማታፀድቅ ገለጸች

ኢትዮጵያ አዲስ የክሪፕቶ ማይኒንግ የኤሌክትሪክ ኃይል ስምምነት እንደማታፀድቅ ገለጸች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር እንደገለጹት ጥያቄውን ለማስተናግድ የኤሌክትሪክ አቅርቦታችን አቅም ማሳደግ እንደሚጠበቅ ገልፀው ይሄን አሁን ባለው አቅም ማስተናገድ እንደማይቻል ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ባለው ዝቅተኛ የታሪፍ ዋጋ እና የኃይል ኃብት በመሳብ 25 ኩባንያዎች የቢትኮይን ማዕድን ቁፋሮ ስራ የጀመሩ ሲሆን፣ 20 የሚሆኑ ኩባንያዎች ደግሞ ፈቃድ ለማግኘት በዝርዝር ተመዝግበው እየጠበቁ ናቸው። ኩባንያው ገቢውን ለማስፋት በማሰብ፣ “ተጨማሪ ኃይል” ብሎ የሰየመውን ጥቅም ላይ ሳይውል የቀረ የኤሌክትሪክ ኃይልን ለክሪፕቶ ማዕድን አውጪ ድርጅቶች በውጭ ምንዛሬ መሸጥ ጀምሮ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ  እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ 25.18 ቴራ…
Read More
ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ተጀመረ

ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ተጀመረ

አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታውቋል። ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የድርጅቱ ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በአንድ ጉዞ 7 ሺህ 500 የኬንያ ሽልንግ ነው የምናስከፍለው። ለደርሶ መልስ ጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ወይም 16 ሺህ ብር ገደማ ያስከፍላል ተብሏል። ከኛ በፊት 'ሮያል አላይድ' የተሰኘ ከናይሮቢ ሞያሌ እና ሞምባሳ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማራ ድርጅት አለ። ከአራት ዓመታት በፊት የተመሠረተው 'ሮያል አላይድ' እስከ ሞያሌ ከተማ ብቻ ይሠራ ነበር። በአውሮፕላን ቲኬት መወደድ ሳቢያ የአውቶብስ ትራንስፖርት ፍላጎት መኖሩን እና ይህንን ፍላጎት ሊያሟላ…
Read More
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው ኤሌክትሪክ ከ118 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው ኤሌክትሪክ ከ118 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 118 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የኤሌክትሪክ ሃይል ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይም ኢትዮጵያ ለኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳንና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል እየሸጠች እንደምትገኝ አብራርተዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመት 25 ሺሕ በላይ ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ 29 ሺሕ በላይ ጊጋ ዋት ሰዓት ማመንጨት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ከተመረተው ኃይል ውስጥም ለኬንያ 85 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ለማከናወን ታቅዶ 86 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡ እንዲሁም ለጅቡቲና ሱዳን ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ28 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ28 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገለጸ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በተቋሙ የበጀት አመት አፈጻጸም ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ጥያቄዎች ተነስተውላቸው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከነዚህም ጥያቄዎች መካከል ከበረራ ትኬቶች ውድነት ጋር እና አየር መንገዱ በኤርትራ ከተያዘበት ገንዘብ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ሲሆን ዋና ስራ አስፈጻሚው ምላሽ ሰጥተውበታል። ከሀገር ውስጥ በረራ ጋር በተያያዘ የ28 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። "የዓለም አቀፍ በረራዎች ትኬት ኮምፒውተር ውስጥ በዶላር ነው የተጻፈው ሰው ትኬት ሲገዛ በእለታዊ የዶላር ምንዛሬ ተመን ነው ይህንን ምንም ልናደርግ አንችልም። የሃገር ውስጥ በረራ ግን በብር ነው የተጻፈው ባለፈው አመት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወቅት አልጨመርንም የዶላር…
Read More