04
Aug
በአማራ ክልል ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ከተጠናቀቀ ዓመት ቢያልፈውም ህገ ወጥ እና የተራዘመ እስር እንደቀጠለ ነው ተባለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳለው ከአማራ ክልል በተጨማሪ በኦሮሚያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያም በወቅታዊ ሁኔታ በሚል ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ አሁንም እየታሰሩ ነው፡፡ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ በየፖሊስ ጣቢያው በተራዘመ እስር ላይ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን ኮሚሽነሩ ብርሃኑ አዴሎ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሌለበት ሁኔታ በወቅታዊ ሁኔታ እያሉ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን መፈፀምም ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በቀጠለው የትጥቅ ግጭት የሰላማዊ ሰዎች በሕይወት የመኖር መብታቸው እየተጣሰ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ለአካላዊ ጉዳት የሚዳረጉ እና ለተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች…