20
Sep
ፓርቲዎቹ "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" የተሰኘ የቅንጅት ፖርቲ መመስረታቸውን ገልጸዋል። ላለፉት ሥስት ዓመታት በትብብር በጋራ ሲሠሩ የቆዩት አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅንጅት መመሥረታቸውን በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል። የቅንጅቱ ስያሜም "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" መሆኑን በዛሬው የመስራች ጉባኤ ላይ ተገልጿል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፖርቲ ፣የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፖርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው ቅንጅት መመሥረታቸውን አስታውቀዋል። ቅንጅቱንም እንዲመሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳንት አቶ አብርሀም ጌጡ ተመርጠዋል። "ለእናት ፖርቲ ትልቅ ቀን ነው" ያሉት የፖርቲው ፕሬዝዳንት ሰይፈስላሴ አያሌው (ዶ/ር)፤ "ኢትዮጵያ 50 ዓመታት የተበታተነ የፖለቲካ ጎራ መከራ እየወረደበት ላለው ፖለቲካ መፍትሄ የሚሰጥ ቅንጅት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በተናጥል የሚመጣ…