ethiopianmedia

የገንዘብ ቀውስ የገጠማቸውን ሚድያዎች ለመታደግ “የመገናኛ ብዙኃን ፈንድ” ሊቋቋም ነው

የገንዘብ ቀውስ የገጠማቸውን ሚድያዎች ለመታደግ “የመገናኛ ብዙኃን ፈንድ” ሊቋቋም ነው

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በገንዘብ ችግር ምክንያት ለመዘጋት የተቃረቡ መደበኛ መገናኛ ብዙኃንን ለመታደግ እና የነፃ ሚዲያ ድምፅ እንዳይቋረጥ የሚያግዝ የመገናኛ ብዙኃን የገንዘብ ድጋፍ ቋት (የሚዲያ ፈንድ) ለማቋቋም የሚያስችል ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል። "የሚቋቋመው ፈንድ ለግልና ለሕዝብ የሚዲያ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል" የተባለ ሲሆን፤ በተለያየ ምክንያት ከሥራ ውጪ በመሆናቸው ገቢያቸው የተቋረጠ ጋዜጠኞችን መታደግ ላይ እንደሚሰራም ተገልጿል። የምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ኃይሉ ባቀረቡት ጥናት፤ በርካታ የሚዲያ ተቋማት በአሁኑ ወቅት በሕትመት ወጪ መናር፣ በሳተላይት ክፍያ ውድነት እንዲሁም በሠራተኞች ደመወዝና የአስተዳደር ወጪ መናር ምክንያት ህልውናቸው አደጋ ውስጥ መግባቱን አብራርተዋል። አቶ ታምራት እንደገለጹት፤ በሰለጠኑት ሀገራት የአንድ ሚዲያ መዘጋት እንደ አንድ…
Read More