26
Feb
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ንጹሃንን ከህግ አግባብ ውጪ ገድሏል ብሏል። ተቋሙ በአማራ ክልል ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ሰፋ ያለ ሪፖርቱን አውጥቷል። በአቡነ ሃራ፣ ልደታ እና ሳባ ታሚት በተባሉ አካባቢዎች ከ17 በላይ ንጹሃን በመከላከያ ተተኩሶባቸው መገደላቸውን ከአይን እማኞች ማረጋገጡን የጠቆመው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳንድ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው ሰዎች አስከሬን መውሰድ እና መቅበር ተከልክለዋል ተብሏል፡፡ ሪፖርቱ በአማራ ክልል የመከላከያ ሰራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ እንደጀመሩና ከሶስት ወር በኋላ በባህር ዳር ተፈጸሙ የተባሉ ግድያዎችን ብቻ የቃኘ ነው። የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋት እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስከተላቸው ክልከላዎች በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በዝርዝር…