AddisAbaba

የአዲስ አበባ እምብርት ከምትባለው ፒያሳ 11 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ከንቲባ አዳነች ተናገሩ

የአዲስ አበባ እምብርት ከምትባለው ፒያሳ 11 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ከንቲባ አዳነች ተናገሩ

በአዲስ አበባ ከፒያሳ እና አካባቢው ከሳምንታት በፊት በተጀመረው የከተማ ማስዋብ ግንባታ ምክንያት 11 ሺህ ሰዎች መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። ከንቲባዋ በሁሉም የመንግስት ሚዲያዎች በተላለፈ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት “በድምሩ ወደ 11 ሺህ ሰው ይሆናል ከዚያ አካባቢ ወደተሻለ ቦታ የወሰድነው” ብለዋል። ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰው በፒያሳ አካባቢ ካሉት ራስ መኮንን ድልድይ፣ ማህሙድ ሙዚቃ ቤት፣ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ፣ አራት ኪሎ የሚገኘው አብርሆት ቤተ መጽሐፍት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ቸርችል ጎዳና ድረስ በሚያካልለው “የኮሪደር ልማት” ምክንያት የተነሱ ናቸው። ይህ የኮሪደር ልማት ከፒያሳ እስከ አራት ኪሎ ባለው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ 8.1 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ከንቲባዋ ገልጸዋል። አዳነች በዚህ ሪፖርት ላይ ከተነሺዎቹ…
Read More
በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ ባሉ 52 ተጠርጣሪዎች ላይ የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ እንዲሁም የሽብር ወንጀሎችን ለመከላከል የወጣውን ህግ ጥሰዋል በሚል ክስ መስርቷል፡፡ በዚህ ክስ መዝገብ ስርም ክርስቲያን ታደለ፣ ዮሀንስ ቧያለው፣ ካሳ ተሸገር (ዶ/ር) ጫኔ ከበደ፣ እስክንድር ነጋ፣ ዘመነ ካሴ፣ አበበ ፈንታው፣ አሰግድ መኮንን፣ መከታው ማሞ፣ ፈንታሁን ሙሃባ እና ሌሎችም ተካተዋል፡፡ ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 14ቱ ተጠርጣሪዎች ልደታ በሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት የቀረቡ ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ እና ቤተሰቦች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ የተጠርጣሪዎች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአልዐይን እንዳሉት በችሎቱ መገኘታቸውን ገልጸው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ማንነት ካረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ትዕዛዞችን…
Read More
መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ለተመልካቾቹ አቀረበ

መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ለተመልካቾቹ አቀረበ

ከመልቲቾይዝ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዲኤስቲቪ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች የተለያዩ መዝናኛ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው ፕሮግራም ከዚህ በፊት የነበሩ እና በቀጣይ ስለሚጀመሩ አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራሞቹን አስተዋውቋል፡፡ በመድረኩ ላይ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖፈጣሪ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ቁጥጥር እና ኮርፖሬት ሃላፊ አቶ መታሰቢያ በላይነህ በመድረኩ ላይ እንዳሉት መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ በየጊዜው አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራም እና ይዘቶችን ያቀርባል ብለዋል፡፡ ድርጅቱ በዚህ ወቅት እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ሲያቀርባቸው ከነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪ አዳዲስ ይዘቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡ በድርጅቱ በኩል ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ይቀርቡ ከነበሩት ይዘቶች በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በአማርኛ እና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ይዘቶች…
Read More
ኢትዮጵያ ከማዕድን ንግድ ከ252 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘሁ አለች

ኢትዮጵያ ከማዕድን ንግድ ከ252 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘሁ አለች

በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከማዕድን ዘርፍ 252 ነጥብ 15 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል። የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፤ በ2016 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ማዕድናት ወደ ውጭ ገበያ በመላክ 252 ነጥብ 15 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ባለፉት ስምንት ወራት ከሁለት ሺህ 673 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ፣ 66 ቶን በላይ ታንታለም እና ከ11 ሺህ 176 ቶን በላይ ሉቲየም ኦር ለውጭ ገበያ መቅረባቸውን ዘርዝረዋል። በተጨማሪም ከ99 ሺህ 021 በላይ ቶን የጌጣጌጥ እንዲሁም 29 ሺህ 281 ቶን በላይ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን አቶ ሚሊዮን ተናግረዋል። የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት…
Read More
18 የዶክትሬት ድግሪ ዩንቨርሲቲ መምህራን ደብዛቸው እንደጠፋ ተገለጸ፡፡

18 የዶክትሬት ድግሪ ዩንቨርሲቲ መምህራን ደብዛቸው እንደጠፋ ተገለጸ፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ላይ መክሯል፡፡ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እና የዩንቨርሲቲው አመራር አባላት በጋራ ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተገለጸው ለሶስተኛ ድግሪ በሚል ለትምህርት የተላኩ እና የጠፉ የዩንቨርሲቲው መምህራን ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እና የፌደራል ዋና ኦዲተር አመራሮች ዩንቨርሲቲው ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርት ብሎ ስፖንሰር ሆኖ የላካቸው መምህራን በወቅቱ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ ዩንቨርሲቲውም ለነዚህ መምህራን የከፈለውን ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር ገንዘብ ለምን ተመላሽ አላደረክም? በሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ከ2011 ዓ.ም…
Read More
ንግድ ባንክ ከተወሰደበት ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ 372 ሚሊዮን ብር ማስመለሱን አስታወቀ

ንግድ ባንክ ከተወሰደበት ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ 372 ሚሊዮን ብር ማስመለሱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ያጋጠመውን የሲስተም ችግር አስመልክቶ እያደረገ ያለውን ስራ የደረሰበት ደረጃ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ፤ ችግሩ የት ጋር ነው ያጠመው የሚለው ላይ በባለሙያ ጥናት እየተደረገ ነው ገና አላለቀም ብለዋል። በእለቱ ከተፈጠረው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ በተደረጉ ግብይች እና የገንዘብ ዝውወሮች ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል። በእለቱ ሊጠፋ የነበረ ወይም አንድ ሰው ገንዘብ ከአካውንቱ ገንዘብ ካስተላለፈ በኋላ ለተላከለትም ሰው ደርሶ ገንዘቡ ለላኪውም ተመለሶ የተተካ ወይም ሪቨርስ ያደረገ 801 ሚሊየን 417 ሺህ 800 ብር  ነበር ብለዋል። በእለቱ አጋጥሞ በነበረ የሲስተም ችግር በነበረበት መስመር ላይ 25 ሺህ 761 ደንበኞች ገብይት ፈጽመዋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤…
Read More
በኢትዮጵያ የወንዴ የዘር ፍሬ መለገስ እንደማይቻል ተገለጸ

በኢትዮጵያ የወንዴ የዘር ፍሬ መለገስ እንደማይቻል ተገለጸ

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ወንዶች የዘር ፍሬያቸውን ሴቶች ደግሞ እንቁላላቸውን መለገስ እንደሚቻል የሚያሳይ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል፡፡ ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው ከሆነ መሰረቱን በትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ከተማ ያደረገ አንድ የህክምና ተቋም የወንድ ዘር ፍሬያቸውን ለሚለግሱ 10 ሺህ ብር እንዲሁም እንቁላላቸውን ለሚለግሱ ሴቶች ደግሞ 30 ሺህ ብር እንደሚከፍል አስታውቋል፡፡ ይህ የህክምና ተቋም ልጅ መውለድ ያልቻሉ ሰዎችን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል ህክምና መጀመሩን እና ለዚህም የተለያዩ መስፈርቶችን አስቀምቷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርን በጉዳዩ ዙሪያ እንዳለው ኢትዮጵያ ከበጎ ፈቃደኞች በተለገሱ የዘር ፍሬዎች አልያም እንቁላል ልጅ እንዲወለዱ የሚፈቅድ ህግ እንደሌላት አስታውቋል፡፡ በሚኒስቴሩ የጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ጸዳል ለአልዐይን እንዳሉት ኢትዮጵያ…
Read More
ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያ ያሉ 70 ሺህ ዜጎቿን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ ነው

ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያ ያሉ 70 ሺህ ዜጎቿን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ ነው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮያውያንን ወደ ሀገራቸው እመልሳለሁ ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ “በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው የመመለስ ሦስተኛ ምዕራፍ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይጀምራል” ብለዋል። በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮያውያንን ለመመለስ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ መክሯል። የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፤ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሥራ በብሔራዊ ኮሚቴው ውስጥ የታቀፉት የፌዴራል ተቋማት እና የክልሎችን የጋራ ቅንጅት ይጠይቃል ብለዋል። ከወዲሁ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በተሟላ ሁኔታ በፍጥነት መጠናቀቅ እንደሚገባቸውም አምባሳደር ብርቱካን ተናግረዋል። አምባሳደር…
Read More
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ህግ ማስከበር እንደማይችል እና የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሀምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የነበረ ሲሆን አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ አይዘነጋም፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንትም ከስድስት ሺህ በላይ የሆኑ ሰራተኞች ስራ ማቆም እና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ከሥራ ውጭ የኾኑ ዜጎች፣ በግጭቱ ምክንያት…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አምስት ተጨማሪ የአገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ። አሁን ላይ አየር መንገዱ 136 ዓለም አቀፍ እንዲሁም 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሉት የጠቆሙት ስራ አስፈጻሚው ተጨማሪ የአገር ውስጥ መዳረሻዎችን ለማስፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አምስት የአገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል።  ኤርፖርቶቹ የሚገነቡት በሚዛን ቴፒ አማን፣ ያቤሎ፣ ጎሬ፣ መቱና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውን ገልጸው፤ አራቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል። ይህም በአገር ውስጥ ያሉ ደንበኞች ፍላጎት ተከትሎ የሚተገበር መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ሌሎች መዳረሻዎችን ጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ ግንባታቸው እንደሚቀጥል ተገልጿል። በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት…
Read More