Dukem

የቱርኩ ኬአርሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአሳንስር ፋብሪካ ለመክፈት ተስማማ

የቱርኩ ኬአርሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአሳንስር ፋብሪካ ለመክፈት ተስማማ

በኢትዮጵያ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፍ የአሳንሰር ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን የተፈራረሙት ሀገር በቀሉ ሞናጎ ኢሊቬተር እና የቱርኩ ኬ አር ሲ ኢሊቬተር መሆናቸው ተገልጿል። ሁለቱ ኩባንያዎች ላለፉት 5 ዓመታት በዘርፉ አብረው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በዱከም ከተማ ማምረቻ ፋብሪካ በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጽመዋል። የ"ሞናጎ" ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ኢሳያስ እንዳስታወቁት፣ ፕሮጀክቱ በዋናነት በሀገሪቱ በሚገኙ ህንጻዎች ላይ የሚታየውን የአሳንሰር ጥገና እና የመለዋወጫ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ያለመ ነው። በጨረታ የሚገዙ አሳንሰሮች ከሽያጭ በኋላ በቂ የጥገና አገልግሎት እና የመለዋወጫ አቅርቦት ስለማያገኙ በተደጋጋሚ ብልሽት እንደሚያጋጥማቸው ተመላክቷል። አዲሱ ስምምነት ይህንን ክፍተት እንደሚሞላው የጠቆሙት…
Read More
በኢትዮጵያ ሶስት ቦታዎች በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በኢትዮጵያ ሶስት ቦታዎች በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በትናንትናው ዕለት በዱከም፣ በወላይታ እና ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሱ ሶስት የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት የ24 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ አደጋዎቹ የደረሱባቸው ኮሙንኬሽን ጽህፈት ቤቶች ባወጡት መረጃ መሰረት የትራፊክ አደጋዎቼ ሰቅጣጭ የሚባሉ ናቸው የተባለ ሲሆን በአጠቃላይ ከ24 ሰዎች ህይወት ማለፍ በተጨማሪ 20 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ዱከም ክፍለ ከተማ የደረሰው የትራፊክ አደጋ አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ደርሷል ተብሏል፡፡ በዚህ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 11 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ ሌላኛው የትራፊክ አደጋ የተከሰተው በአዲሱ ማዕከላዊ…
Read More