24
May
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን በከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ ዋንጫን አነሳ፡፡ ከሁለት ጨዋታዎች በፊት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ሀ የከፍተኛ ሊግ ውድድር የመዝጊያ ስነ-ሥርዓት ላይ ዋንጫውን አንስቷል፡፡ ቡድኑ ቀሪ የመርሐ ግብር ጨዋታውን ከቀኑ 6፡00 ላይ ከሰንዳፋ በኬ ጋር በማድረግ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ነጥቡን 60 ማድረስ ችሏል፡፡ በውድድሩ የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመርቻንት እና ኤጀንት ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ብሌን ኃ/ሚካኤል እና ሌሎች እንግዶች ለሻምፒዮኑ ቡድን እና ለሌሎች ተሸላሚዎች…