13
Aug
ለ17 ቀናት በፓሪስ የተካሄደው 33ኛው ኦሎምፒክ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል። በፓሪስ ኦሎምፒክ ድል ያስመዘገቡ እና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብተዋል። የልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ለልዑካን ቡድኑ የክብር ሽልማት፣ የማበረታቻ እና የእራት ግብዣ መርኃ-ግብር የሚካሄድ መሆኑንም ተገልጿል። ኢትዮጵያ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ 1 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም 47ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል። ታምራት ቶላ በማራቶን ወርቅ፣ ጽጌ ድጉማ በሴቶች 800 ሜትር ብር፣ በሪሁ አረጋዊ በወንዶች 10 ሺህ…