30
Jun
አሜሪካ ኢትዮጵያን ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ ሀገርነት ዝርዝር ውስጥ ሰርዛለች። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር አሜሪካ ኢትዮጵያን የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ ሀገር ዝርዝር ውስጥ የመዘገበቻት። ይህን ተከትሎም ዋሽንግተን ለኢትዮጵያ ታደርጋቸው የነበሩ የልማት ስራዎች ድጋፎችን አቋርጣ ቆይታለች። እንደ ፎሬይን ፖሊሲ ዘገባ ከሆነ አሜሪካ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምባት ሀገር አይደለችም የሚል አቋም ላይ ደርሳለች። በኮሮና ቫይረስ፣ በጦርነት እና በዓለም አቀፍ ንግድ መቀዛቀዝ ምክንያቶች ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ሀገራት የብድር መክፈያ ጊዜ ሽግሽግ እንዲደረግ አስቀድማ ጠይቃ ነበር። ይሁንና አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በጣለችው እገዳ ምክንያት ዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ ለብዙ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ያደረጉትን የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ማድረግ…