03
Apr
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት ጋር እያደረገችው ያለው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋሙ አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይቶችን ከሚያደርጉ አበዳሪ ተቋማት መካከል ዋነኛው ሲሆን ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ቆይታ አድርጎ መመለሱ ተገልጿል፡፡ አይኤምኤፍ በድረገጹ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ መሰረት ከመጋቢት 10 እስከ 24 ቀን 2016 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ ቆይታ አድርጎ ተመልሷል፡፡ ኢትዮጵያ ልታካሂደው ባሰበችው የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ አይኤምኤፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ እንዳቀረበች የገለጸው ይሄው ተቋም በአልቫሮ ፒሪስ የተመራ የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች ቡድን ወደ አዲ አበባ መምጣቱን አስታውቋል፡፡ ለ15 ቀናት በዘለቀው በዚህ የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች ቡድን እና የኢትዮጵያ ባለሙያዎች እና ባለስልጣናት መካከል የተደረገው ውይይት ገንቢ እንደነበርም ተገልጿል፡፡…