04
Feb
ከአማራ ክልል ዋና ከተማ ከሆነችው ባህርዳር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው መራዊ ከተማ ከሰሞኑ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ ተቀስቅሶ ነበር፡፡ በዚህ ውጊያ ምክንያት የፋኖ ታጣቂዎች የመራዊ ከተማን ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም በኋላ ለቀው መሄዳቸውን ተከትሎ ወደ ከተማው የገባው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ50 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎችን እንደገደሉ ቢቢሲ ነዋሪዎችን አነጋግሮ ዘግቧል፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ አስተያየት ከሆነ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነዋሪዎቹን ከመንገድ ላይ እና መኖሪያ ቤታቸው በማሰባሰብ ገድለዋቸዋል፡፡ በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን የፋኖ ታጣቂዎች በተለይም የገጠር አካባቢዎችን ተቆጣጥረው ሲያዙ ከተሞች ደግሞ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተይዘዋል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት…