09
Jun
የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መፅሀፍ የፃፈችው ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት። ረዳት ፀሀፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲሚ የተባለ ፀሀፊ መሆኑን ሰምተናል። በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሀፍ ለማሳናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሀፊዋ አስረድታለች። አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መፃህፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተነግሯል። ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሀይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ጠቅሳለች። መፅሀፉ አትሌት ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፣ ፍልስፍናውን፣ የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ልጁ ሜላት ተናግራለች። ለጊዜው ''Dissecting Haile' በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መፅሀፋ ወደፊት ወደ ወደ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል።…