19
Apr
በኢትዮጵያ በፀጥታ ችግር ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት 8,977 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 6,483 ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ 'ትምህርትን በአደጋ ማስቀጠል' ባለሙያ ንጋቱ አበበ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስቴሩ እና የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል ጥረት ቢያደርጉም፤ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች በቀጠሉት ግጭቶች ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ እንደሆነ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ባለሙያው ጥሪ አቅርበዋል። ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት እየተካሄደ ባለበት የአማራ ክልል ውስጥ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን…