17
Apr
በፌደራል መንግስት እና የትግራይ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደው እና ለሁለት ዓመት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ በተፈረመ የሰላም ስምምነት መቆሙ ይታወሳል፡፡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ጦርነት ተፋላሚዎች ወደ ተኩስ አቁም እንዲሄዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት ቡድን ሰባት፣ ብሪታንያ እና ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት በጋራ እና በተናጠል የተለያዩ ጫናዎችን ሲያደርጉ ነበር፡፡ ጦርነቱ በፍጥነት ባለመቆሙ ምክንያትም ሀገራት በኢትዮጵያ ያላቸውን ፕሮግራሞች ማቋረጥ፣ ቢሮ መዝጋት፣ እንደ አግዋ ኤነት ለኢትዮጵያ ተሰጥተው የነበሩ የገበያ እድሎችን መከልከል፣ ተፈቅደው የነበሩ ብድሮችን መከልከል እና የቀጥታ በጀት ድጋፎችን ማቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ ከተደረጉ ጫናዎች ዋነኞቹ ነበሩ፡፡…