Surgery

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ3 ሺህ በላይ ህጻናት ከከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ3 ሺህ በላይ ህጻናት ከከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የከንፈር እና ላንቃ ስንጥቃት ላጋጠማቸው ህጻናት ድጋፍ በማድረግ ዘርፍ የተሰማራው "ስማይል ትሬን" የተሰኘው ተቋም ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መስራት ከጀመረ ከ20 በላይ ሆኖታል። ድርጅቱ ከሌላኛው ዓለም አቀፍ የጤና ተቋም ላይፍ ቦክስ ከተሰኘው ተቋም ጋር በመቀናጀት ደህንነቱ የተጠበቀ የቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። እነዚህ ሁለት ተቋማት ቲም ክሌፍት ከተሰኘ የሀገር በቀል ድርጅት ጋር በመቀናጀት የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ያጋጠማቸው ህጻናትን የቀዶ ጥገና ህክምና ለሚሰጡ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል። ዶ/ር ቤቴል ሙልጌታ የስማይል ትሬን ምስራቅ አፍሪካ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ እርሳቸው የሚመሩት ቢሮ በኢትዮጵያ ካሉ ከ20 በላይ የግል እና የመንግስት ሆስፒታሎች ጋር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ…
Read More