ዜና

የሶስት ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከስልጣን ተነሱ

የሶስት ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከስልጣን ተነሱ

ትምህርት ሚኒስቴር ከገንዘብ ብክነት ጋር በተያያዘ የሶስት ዩንቨርሲቲዎችን ፕሬዝዳንት ከሀላፊነት አንስቷል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት እንደተገለፀው ዩንቨርሲቲዎች የበጀት ብክነት ፈጽመዋል ተብሏል። የወላይታ ሶዶ፣ የጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲፕሬዝዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ትምህርት ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር ባደረገው የስራ ግምገማ ወቅት አስታውቋል፡፡ለአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች አራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሠራው የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 13 ተቋማት ላይ አስተደደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ…
Read More
በአማራ ክልል ጎጃም ሰከላ 40 ንጹሃን ነዋሪዎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ጎጃም ሰከላ 40 ንጹሃን ነዋሪዎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ከግንቦት 5 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ 40 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ንጹሃኑን የገደሉት ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የነበሩ እና የሰርግ ስነስርዓትን ታድመው ሲመለሱ እንደሆነ አሻም ቲቪ ዘግቧል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች እንዳሉት በአካባቢው ከዚህ ቀደም ብሎ ግንቦት 4 በፋኖ ሀይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ እንደነበር ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም በስጋት ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ባህርዳር እና ወደ ሌሎች ገጠራማ አካባቢዎች መሰደዳቸውን ተናግረዋል። የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ እድሜአለም አንተነህ በበኩላቸው በአካባቢው ውጊያ እንደነበር ገልፀው ነገርግን አንድም ንፁሃን አልተገደለም ማለታቸውን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በአማራ…
Read More
ዘጠኝ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ህጻናት ከትምህርት ገባታ ውጭ መሆናቸው ተገለጸ

ዘጠኝ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ህጻናት ከትምህርት ገባታ ውጭ መሆናቸው ተገለጸ

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 85 ሚሊየን ህጻናት በትምህርት ገበታ ላይ አይገኙም ብሏል። የሀገሪቱ የትምህርት ሁኔታ አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያለው ዩኒሴፍ ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በሀገሪቱ በበርካታ ቦታዎች እየተባባሰ የመጣው ግጭት ነው ሲል ጠቁሟል። በተያዘው የፈረንጆቹ አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት (ጥር፣ የካቲትና መጋቢት) በሀገሪቱ የተዘጉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር በ18 በመቶ ጨምሯል ያለው ዩኒሴፍ ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ቤቶችን ቁጥር በ5 ነጥብ 5 በመቶ መጨመሩንም ጠቁሟል። በሀገሪቱ 6 ሺ 770 ትምህርት ቤቶች ጉዳት ሲደርስባቸው 6 ሺ 410 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ተዘግተዋል ሲል በየሶስት ወሩ በትምህር ዙሪያ በሚያሳትመው ኒውስሌተር ላይ ባሰፈረው ሪፖርት አስታውቋል። በትምህርት ገበታ ላይ…
Read More
ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቶች ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርቡ ፈቀደች

ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቶች ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርቡ ፈቀደች

ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እና የውጪ ንግድን ለማሳደግ በሚል ነበር ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የገነባችው፡፡ አሁን ላይ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሏት ኢትዮጵያ ፓርኮች የምርታቸውን 50 በመቶ ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ፈቅዳለች፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ገበያ እንጂ ለሀገር ውስጥ ማቅረብ ሳይፈቀድላቸው መቆየቱን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ገልጸዋል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተጽዕኖ ሥር የነበሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት በፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ በአዋጅ መፈቀዱን አስታውቀዋል። ከሁለት ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ አሜሪካ…
Read More
ኢትዮጵያ ከብድር እና እርዳታ ከአራት ቢሊዮን በላይ ዶላር ማግኘቷን አስታወቀች

ኢትዮጵያ ከብድር እና እርዳታ ከአራት ቢሊዮን በላይ ዶላር ማግኘቷን አስታወቀች

የገንዘብ ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት እቅዱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስቴሩ ባቀረበው የፋይናንስ ሪፖርቱ ላይ እንዳለው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከብድር እና እርዳታ 4 ነትብ 5 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ብሏል፡፡ ከተገኘው ከዚህ ውስጥ 54 በመቶው ዕርዳታ ነው የተባለ ሲሆን 849 ሚሊዮን ዶላር በብድር የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ከተገኘው ገቢ ውስጥም የዓለም ባንክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ፈሰስ አድርጓል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላትም አስታውቃለች፡፡ ከሀገር ውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ 356.5 ቢሊዮን ብር ለመሰብስብ ታቅዶ 338 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደተሰበሰበም ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ወደ ግል ይዞታ ከተዛወሩ የመንግስት ድርጅቶች በዘጠኝ ወር ውስጥ ከወቅታዊ እና ከውዝፍ ዕዳ ብር…
Read More
በኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠጥል ተነገረ

በኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠጥል ተነገረ

የኢትዮጰያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በቀጣዮቹ አሥር ቀናት ውስጥ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እንደሚያመላክቱን በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሰፊ ቦታዎችን ያካተተና የተጠናከረ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተስፋፋ ዝናብ የሚኖር ሲሆን እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጲያ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸውም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡ በአጠቃላይ በሚቀጥሉት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፤ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፤ ነአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች …
Read More
ኢትዮጵያ በሀርጌሳ ያለው የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ወደ ኤምባሲ አሳደገች

ኢትዮጵያ በሀርጌሳ ያለው የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ወደ ኤምባሲ አሳደገች

ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ፣ ሃርጌሳ የሚገኘውን የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ሙሉ አገልግሎት ወደሚሰጥ ኤምባሲ ማሳደጓን የሶማሊላንድ ሚኒስትር ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በወደብ ጉዳይ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት እንድትሆን ሶማሊላንድ ደግሞ የሀገርነት እውቅና እንድታገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና እና ተቃውሞን አስከትሏል። ከአንድ ወር በፊት ሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደርን በ72 ሰዓት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ እና በሀርጌሳ እና ጋሮዌ ያሉ የቆንሱላ ጽህፈት ቤቶች እንዲዘጉ ሰራተኞቹም በሁለት ሳምንት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን አስታውቃ ነበር፡፡ በወቅቱም ራስ ገዟ ሶማላንድ…
Read More
ኢትዮጵያ አዲስ የነዳጅ ማደያ ፈቃድ መስጠት አቆመች

ኢትዮጵያ አዲስ የነዳጅ ማደያ ፈቃድ መስጠት አቆመች

በመላው ሃገሪቱ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱ ተገለጿል፡፡ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አሁን ላይ የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያ ፍቃድ ሙሉ ለሙሉ አስታውቋል፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ እንደተናገሩት መንግስት የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያን የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡ መንግስት የነዳጅ ማደያዎችን በሀገር ውስጥ ለማስፋፋት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ አሁን ላይ ግን ባልተፈለገ አቅጣጫ እየሄደ መሆኑን ባለስልጣኑ በማረጋገጡ ፍቃዱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ባለስልጣኑ ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ወ/ሮ ሳህረላህ የማደያዎች ፍቃድ አሰጣጥ እና ተደራሽነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ካገኙ በኋላ ፍቃድ የመስጠቱ ስራ ዳግም እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ከተፈታ በኋላ በተለይም የነዳጅ…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ የመከላከያ ሚኒስሩን ከስልጣን አነሱ

ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ የመከላከያ ሚኒስሩን ከስልጣን አነሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አብርሀም በላይ (ዶ/ር) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነው ተሸመዋል፡፡ እንዲሁም አይሻ መሀመድ በአብርሀም በላይ ምትክ የሀገር መከላከያ ሚንስትር እንዲሁም የዲያፖራ ባለስልጣን ዳይሬክተር የነበሩት መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ተደርገው ተሹመዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአመራር ሽግሽግ ለምን እንዳደረጉ በይፋ ያላሳወቁ ሲሆን በአማራ ክልል የሚገነቡ የመስኖ ግድቦች በወቅቱ አለመጠናቀቃቸውን እና የገንዘብ ብክነት ማጋጠሙን ጉብኝቱን ባካሄዱበት ባሳለፍነው ሳምንት መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሁለት ወር በፊት ደህንነት እና ዲፕሎማሲን ጨምሮ በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ የአመራር ሽግሽግ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚልየን ዶላር ያስገነባውን የመንገደኞች ማስተናገጃ አስመረቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚልየን ዶላር ያስገነባውን የመንገደኞች ማስተናገጃ አስመረቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ50 ሚልየን ዶላር ያስገነባውን አዲስ የአገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ዛሬ አስመረቀ። በአየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የአገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከአገር ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ለሚደረጉ በረራዎች በዚህ ተርሚናል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አዲሱ የአገር ውስጥ ተርሚናል አየር መንገዱ የሚሰጠውን የአገር ውስጥ በረራ አቅም በዕጥፍ እንደሚያሳድገው አስታውቀዋል። አየር መንገዱ 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት። የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አዲስ የተገነባው የአገር ውስጥ ተርሚናል የቱሪዝም ዘርፍ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል። አየር መንገዱ ከሁለት ወራት በፊት በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የድጅታል ግብይት…
Read More