ዜና

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸው ተሰማ

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸው ተሰማ

ፖለቲከኛው የሺዋስ አሰፋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት አንድ ሰዓት ካዛንቺስ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡ የኢህአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አብርሃም ሃይማኖት ለአሻም እንዳሉት የሺዋስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የህዳር 30 ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ውስጥ አንደኛው የሆኑት ናትናዔል መኮንን በዛሬው እለት  ከእስር ተፈቷል። የሺዋስ አሰፋ የህዳር 30 ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ሲሆኑ ሰልፉ ከመካሄዱ ሦስት ቀናት በፊት (ህዳር 27) ከአስተባባሪዎቹ መካከል አብርሃም ሃይማኖት፣ ጊደና መድህን፣ ናትናዔል መኮንንን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞችና የህግ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ አቶ የሺዋስ ግን አልታሰሩም ነበር። ህዳር 27 በቁጥጥር ስር…
Read More
ዲኤስቲቪ በአንጋፋው የአፍሪካ መዝናኛ ፕሮግራም መሪ ኖሎ ሌተሌ ላይ ያተኮረ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሊያሳይ ነው

ዲኤስቲቪ በአንጋፋው የአፍሪካ መዝናኛ ፕሮግራም መሪ ኖሎ ሌተሌ ላይ ያተኮረ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሊያሳይ ነው

አፍሪካ በአለምአቀፍ የብሮድካስት መዝናኛ ኢንደስትሪ ውስጥ ያላትን ቦታ እንዲረጋገጥ ባለፉት 50 ዓመታት የተሰሩ እንቅስቃሲዎች ላይ ትኩረቱን ያደረግውና በተለይም የቀድሞ የመልቲቾይስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ለረጅመ ጊዜ ያገለገሉት ኖሎ ሌተሌ አስተዋዎ የሚቃኝው አዲስ ዘጋቢ ፊልም “አዎ ለማይቻለው፣ የኖሎ ሌተሌ ታሪከ ” በሚል ርዕስ ተዘጋጀቶ ለእይታ ሊበቃ ነው፡፡  ዘጋቢ ፊልሙ በመላው አፍሪካ ነፃነት ለማግኘት የሚደረጉ እንቅስቃሲዎች በተንሰራፋበት ወቅት በታዳጊ ዕድሚ ላይ የነበሩት ኖሎ አህጉሪቱ የራሷ የሆነ ድምጽ እንዲኖራት የነበራቸውን ራዕይ እንዴት እንደቀረፁት ፣ ይህንንም ራዕይ እውን ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውነ ያላሰለሰ ጥረት እና ረጅም ጉዞ በጥልቀት የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ በሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪከ ምህንድስና ትምህርት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በዚያን ጊዜ የአፓርታይድ ስርዓት የምትከተለው…
Read More
ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአውሮፓ ህብረት ሹማን ሽልማትን አሸነፉ

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአውሮፓ ህብረት ሹማን ሽልማትን አሸነፉ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደ የሽልማት ሥነ ሥርዓት የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት (Schuman EU Awards) ተበርክቶላቸዋል፡፡ ሽልማቱ በኢትዮጵያ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን ለመጀ ሽልማቱ “ዴሞክራሲን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ መቻቻልን እና እኩልነትን በማስፋፋት ረገድ የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሰዎች” ዕውቅና የሚሰጥ ነው ተብሏል። የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ የተበረከተው እ.ኤ.አ. በ2017 በምያንማር የኅብረቱን 60ኛ ዓመት ምሥረታ በማስመልከት ነበር። ሽልማቱ ሰዎችን ለማበረታታት እና ተግባቦትን በማጠናከር ዲፕሎማሲን በተሻለ መንገድ ለመከወን ያለመ ሲሆን የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር “የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የአውሮፓ ኅብረትን በአንድነት ከሚያቆሙት ጉዳዮች…
Read More
ኢትዮጵያ ከአበባ ንግድ ከ300 ሚሊዮን  ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከአበባ ንግድ ከ300 ሚሊዮን  ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ባለፋት አስር ወራት ከአበባ ኤክስፓርት ከ 3 መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች፡፡ የሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ዘርፍ በተለይም የአበባ ኤክስፖርት ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦን  እያበረከተ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት እና ምርት ግብይት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ አበበ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፋት አስር ወራት 79 ሺህ 819 ቶን የአበባ ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ 392 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች ብለዋል። የኢትዮጵያ የአበባ ምርት በአብዛኛው ወደ አውሮፓና ኤዥያ ሀገራት እንደሚላክ  የተናገሩት   ስራ አስፈፃሚው  ምርጥ አስር ተብለው ከተለዩት ተቀባይ ሀገራት መካከል ደግሞ ኔዘርላንድ ትልቁን ድርሻ ትይዛለች ብለዋል።  በበጀት አመቱ አስር ወራት ከእቅድ አፈፃፀም አንጻር ሲታይ የተገኘው ገቢ…
Read More
ኢትዮጵያ ህገ ወጥ የወርቅ ግብይትን ማስቆም እንዳልቻለች ተገለጸ

ኢትዮጵያ ህገ ወጥ የወርቅ ግብይትን ማስቆም እንዳልቻለች ተገለጸ

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወርቅ ማዕድን 363 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ያቀደች ቢሆንም የተገኘው ግን 67 በመቶው ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ህገ ወጥ የወርቅ ግብይት ዋነኛው ችግር መሆኑን ተከትሎ በመከላከያ ኮማንድ ፖስትና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጭምር ክትትል ቢደረግም ህገ ወጥ የወርቅ ንግድን ማስቆም እንዳልተቻለ ማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በማዕድናት ሕገ ወጥ ግብይት፣ ኮንትሮባንድና የፀጥታ ችግር ምክንያት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ ሦስት ቶን ብቻ እንደሆነ፣ ይህም ከዕቅዱ 50 በመቶ ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡ በመጋቢት ወር ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ 350 ኪሎ ግራም ሲሆን ይህም በ2014 መጋቢት ወር ከተገኘው 800 ኪሎ ግራም በእጅጉ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡ በአገሪቱ ያሉ ወርቅ…
Read More
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት መንግስት ታህሳስ እና ግንቦት ላይ በፈጸማቸው ሁለት የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች ሲገደሉ ከ10 በላይ ቆስለዋል ብሏል፡፡ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ባወጣው የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ሲሆን አሁንም ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፣ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እጅግ አሳሳቢ ሆነው የቀጠሉ የመብት ጥሰቶች መሆናቸው ተገልጿል። ኮሚሽኑ በጸጥታ ችግር እና ከመንግስት ተገቢውን ትብብር ባለማግኘት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች…
Read More
መንግስት በአማራ ክልል የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ ተጠየቀ

መንግስት በአማራ ክልል የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ ተጠየቀ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በኢትዮጵያ እንደ አዲስ እየተባባሱ የመጡት የሲቪክ ምህዳሩን የሚያጣብቡ ድርጊቶች እንዳሳሰቡት አስታውቋል። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን “መልሼ አደራጃለሁ” የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ቀርቶታል። ይኼውም የጸጥታ እና ደህንነት አካላት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምርመራ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን እያዋከቡ ከመሆኑንም ባሻገር በቲያትር እና…
Read More
አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የአሜሪካ አምባሳደር ተደርገው ሊሾሙ ነው ተባለ

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የአሜሪካ አምባሳደር ተደርገው ሊሾሙ ነው ተባለ

በዋሸንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ስለሺ በቀለ የስልጣን መልቀቂያ አስገብተዋል በአሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ አምባሳደር ሽለሺን ይተካሉ ተብሏል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ  ከተሾሙበት የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ። ስለሺ በቀለ  በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት መዋቅር በመልቀቅ በግል ተቀጥረው በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። አምባሳደር ስለሺ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን ወቅት የፓርቲ አባል ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው…
Read More
ኩዌት ኢትዮጵያዊን ሰራተኞችን ለመቅጠር ተስማማች

ኩዌት ኢትዮጵያዊን ሰራተኞችን ለመቅጠር ተስማማች

ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ፈርመውታል። በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤል ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስምምነቱ ወደ ኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ህጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ እንደሚፈጥር ተገልጿል። በነዳጅ የበለጸገችው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር ኩዌት የሦስት ወራት አስገዳጅ ስልጠና የወስዱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን…
Read More
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ በመንግስት ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ በመንግስት ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ገለጸ

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ላይ የሚደረገው ወከባ እና እስር እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጠይቋል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መንግስት ከፍተኛ ጥቃትና ጫና እየፈጸመበት እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡ ኢሰመጎ በመግለጫው በመንግስት እየደረሰበት ያለው ጥቃት እና ጫና አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጫው ላይ አሳውቋል። ጉባኤው በተለያዩ ጊዜ ተፈጽመውብኛል ያላቸው ጥቃቶች እና ከፍተኛ ጫናዎች በመግለጫው ላይ የዘረዘረ ሲሆን በተቋሙ አመራር ላይ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የሚፈጸም ክትትል ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየጨመረ መምጣታቸውን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ክትትል ስራችሁን ካላቆማችሁ ፤ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት መወንጀል ካላቆማችሁ  ' ዋጋ ትከፍላላችሁ ' የሚል ዛቻ እየደረሰበት መሆኑን ገልጿል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርመራ ስራ በሚሰሩ…
Read More