Danielbekele

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአውሮፓ ህብረት ሹማን ሽልማትን አሸነፉ

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአውሮፓ ህብረት ሹማን ሽልማትን አሸነፉ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደ የሽልማት ሥነ ሥርዓት የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት (Schuman EU Awards) ተበርክቶላቸዋል፡፡ ሽልማቱ በኢትዮጵያ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን ለመጀ ሽልማቱ “ዴሞክራሲን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ መቻቻልን እና እኩልነትን በማስፋፋት ረገድ የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሰዎች” ዕውቅና የሚሰጥ ነው ተብሏል። የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ የተበረከተው እ.ኤ.አ. በ2017 በምያንማር የኅብረቱን 60ኛ ዓመት ምሥረታ በማስመልከት ነበር። ሽልማቱ ሰዎችን ለማበረታታት እና ተግባቦትን በማጠናከር ዲፕሎማሲን በተሻለ መንገድ ለመከወን ያለመ ሲሆን የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር “የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የአውሮፓ ኅብረትን በአንድነት ከሚያቆሙት ጉዳዮች…
Read More