27
May
በዋሸንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ስለሺ በቀለ የስልጣን መልቀቂያ አስገብተዋል በአሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ አምባሳደር ሽለሺን ይተካሉ ተብሏል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ ከተሾሙበት የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ። ስለሺ በቀለ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት መዋቅር በመልቀቅ በግል ተቀጥረው በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። አምባሳደር ስለሺ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን ወቅት የፓርቲ አባል ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው…