26
May
ትምህርት ሚኒስቴር ከገንዘብ ብክነት ጋር በተያያዘ የሶስት ዩንቨርሲቲዎችን ፕሬዝዳንት ከሀላፊነት አንስቷል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት እንደተገለፀው ዩንቨርሲቲዎች የበጀት ብክነት ፈጽመዋል ተብሏል። የወላይታ ሶዶ፣ የጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲፕሬዝዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ትምህርት ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር ባደረገው የስራ ግምገማ ወቅት አስታውቋል፡፡ለአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች አራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሠራው የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 13 ተቋማት ላይ አስተደደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ…