ዜና

ኢትዮጵያ ለሕጋዊ የዱር እንስሳት አደን እስከ 15 ሺህ ዶላር እያስከፈለች መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ ለሕጋዊ የዱር እንስሳት አደን እስከ 15 ሺህ ዶላር እያስከፈለች መሆኗን ገለጸች

የዱር እንስሳትን ማደን የሚፈልጉ ጎብኚዎች በመላው ዓለም ያሉ ሲሆን አፍሪካ ዋነኛ የዱር እንስሳት አዳኞች መዳረሻ ናት፡፡ ናሚቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ሞዛምቢክ እና ደቡብ አፍሪካ ዋነኛ የዱር እንስሳት ማደንን በሚፈልጉ ጎብኚዎች የሚጥለቀለቁ ሀገራት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያም የዱር እንስሳትን ለህጋዊ አደን ከሚያዘጋጁ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ለዚህ የሚረዳ አሰራር መዘርጋቷን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ዴስክ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ወርቁ ለአል ዔን እንዳሉት ኢትዮጵያ በአራት ክልሎች ሕጋዊ የዱር እንስሳት አደን በማካሄድ ላይ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ፣ አፋር፣ ሶማሊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ክምላው ዓለም ለሚመጡ ጎብኚዎች ሕጋዊ የዱር እንስሳት አደን እየተካሄደ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለሕጋዊ አደን የተፈቀዱ…
Read More
ቴክኖ ሞባይል ካሞን 30 ፕሮ 5G የተሰኘ አዲስ ስልክ ይፋ አደረገ

ቴክኖ ሞባይል ካሞን 30 ፕሮ 5G የተሰኘ አዲስ ስልክ ይፋ አደረገ

ቴክኖ አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው አመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጲያ አስተዋወቀ። የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋውቋል፡፡ አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው። ቴክኖ በቅርቡ በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው አንጋፍው እና አመታዊው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን (Mobile World Congress) ላይ ይህን አዲስ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በይፋ እንዳስተዋቀ የሚታወቅ…
Read More
ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙንኬሽን ሳተላይት ባለመያዟ ምክንያት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች መሆኗ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል በሚል ነበር መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁት፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጥያቄውን ተቀብሎ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡ ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል በሚል ለቴሌቪዥን ባለንብረቶች ያሳውቃል፡፡ በዚህ መሰረትም 70ዎቹ ስርጭታቸውን በኢትዮሳት በኩል ያደረጉ ሲሆን ዓመታዊ ወጪያቸው ግን እንዳልቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ብሮድካስተሮች ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ወጪ ለመቀነስ ብለው ወደ ኢትዮሳት የገቡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዓመት ለሳተላይት ስርጭት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት…
Read More
ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋዜማ ሬዲዮ፣ ኢኤምኤስ እና ሌሎችም ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ከተማ "ሕገ ወጥ ግንባታ" ናቸው ተብለው በፈረሱ ወደ 100 ሺህ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችና በተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ለዘገባ ወደ ስፍራው ባመራበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ለእስር ተዳርጎም ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በፖሊስ ድብደባ፣ እስርና ማዋከብ ደርሶበት እንደነበር የተናገረው ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋስ ከእስር ቤት ወጥቶ እንዲከራከር በፍርድ ቤት ተወስኖለት ቢወጣም ዛቻና ማስፈራሪ ሲደርስበት እንደነበረ ለኢትዮ ነጋሪ ተናግሯል፡፡ በቅርቡም ለዋዜማ ሬድዮ እና ኢንተር ኒውስ ዘገባ ለመስራት ወደ አማራ ክልል ደሴና ሐይቅ ከተሞች በተጓዘበት ወቅት በክልሉ ኮማንድ ፖስት ታስሮ እንደነበረም አክሏል። አስቀድሞ በታሰረበት ጉዳይ ለዋስትና የተያዘውን ገንዘብ…
Read More
አሜሪካ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጠየቀች

አሜሪካ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጠየቀች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ የሚገኘውን የአሜሪካ ግቢ ጎብኝተዋል። አምባሳደሩ በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉት የአሜሪካ ግቢ ከ87 አመት በፊት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ከሞት ማምለጫ መሆኑን አውስተዋል። የካቲት 12 1929 ዓ.ም ፋሺስት ጣሊያን በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት ጭፍጨፋ ሲፈጽም አሜሪካዊው ዲፕሎማት ኮርኔልስ ቫን ኤንገርት ከ750 በላይ ኢትዮጵያውያን በኤምባሲው ውስጥ እንዲደደበቁ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያውያን ከ87 አመት የሰውነት ክብራቸው ተጥሶ በህይወት የመኖር መብታቸው ሲነጠቅ ታይቷል ያሉት አምባሳደሩ የሞራል ልዕልና እና ሰብአዊነት ካላቸው ኮርኔልስ ቫን ኤንገርት ልንማር ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል። ከ87 አመት በኋላም በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሀገራት የሰው ልጆች ክብር እና በህይወት የመኖር መብት በታጣቂዎች፣ ዘራፊ ቡድኖች እንዲሁም በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መጣሳቸው…
Read More
ኦቪድ ግሩፕ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የገነባቸውን 248 መኖሪያ ቤቶች አስረከበ

ኦቪድ ግሩፕ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የገነባቸውን 248 መኖሪያ ቤቶች አስረከበ

ኦቪድ ግሩፕ እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትን አጠናቀዋል፡፡ ኦቪድ ግሩፕ እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ታሪካዊ በሆነ ትብብር በኮዬ ፈጬ የገነቡትን የቤት ፕሮጀክት አጠናቀው አስረክበዋል፡፡ በ16 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና ዘመናዊ የሆኑ የመኖሪያ ቤት አገልግሎቶችን አሟልተዋል የተባሉት እነዚህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ጥራታቸውን ጠብቀው መገንባታቸው ተገልጿል፡፡ ኮዬ ፈጬ አካባቢ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፤ አራት G+7  እና ሦስት G+9 ሕንጻዎችን፤ በድምሩ ሰባት ሕንጻዎችን የያዘ ሲሆን፤ 120 ባለ ሦስት መኝታ እና 128 ባለ አራት መኝታ፤ በአጠቃላይ 248 የመኖሪያ ቤቶች አሉት። ግንባታው ወደ የትኛውም ሕንጻ የሚያደርሱ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን እና ለምለም አረንጓዴ ቦታዎችን ያካተተ እና የኑሮ ደረጃን ትኩረት አድርጎ፤ ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆን ታስቦ በልዩ…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መመዝገቢያ ጊዜን አራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መመዝገቢያ ጊዜን አራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም.  ምርጫ ለማከናወን የተለያዩ ዝግጅቶችን  በማድረግ ላይ ይገኛል። ቦርዱ ከሚያዝያ 21 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ነገር ግን የመራጮች ምዝገባ በወጣበት የጊዜ ሰሌዳ ወቅት ተደራራቢ የህዝብና የሃይማኖት በዓላት የነበሩ በመሆኑ፣ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸው አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱ ባለመከፈታቸውና በምርጫ የሚወዳደሩት የፓለቲካ ፓርቲዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ ቀን እንዲራዘም በመጠየቃቸው ቦርዱ የመራጮችን የምዝገባ ቀን እስክ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ማራዘሙን…
Read More
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ተገደሉ

አንድ ዓመት ባስቆጠረው የአማራ ክልል የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ግጭት መቋጫ አላገኘም፡፡ በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጉሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የተሬ ቀበሌ ነዋሪ እንዳለው “ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በመንደራችን ከባድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ የሰፈራችን ነዋሪዎች ፍንዳታው ወደ ተሰማበት ስፍራ ስንሄድ ጥቃቱ ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደተፈጸመ አየን” ሲል ተናግሯል፡፡ አስተያየት ሰጪው አክሎም “በዚህ የድሮን ጥቃት ሶስት አርሶ አደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት…
Read More
ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የላሙ ወደብን ለማልማት እና ለመጠቀም በ2001 ዓ.ም በወቅቱ የኬንያ ፕሬዝዳንት፣ ሞ ኪባኪ፣ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት አማካኝነት ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል፡፡ ኬንያ ይህን ፕሮጀክት በማልማት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን እንዲጠቀሙበት ፍላጎት ያላት ቢሆንም ኢትዮጵያ እስካሁን ፍላጎት እንዳልነበራት ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያ ተጨማሪ የገቢ ወጪ ንግድ አማራጭ ወደብ እንዲኖራት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ሲሆን የላሙ ወደብን አንዱ አማራጭ አድርጎ ለመጠቀም መወሰኑ ከወራት በፊት መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ ስምምነት ከተፈረመ ከ15 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀምራለች፡፡ "ዓባይ" የተሰኘችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ግንቦት 3 ቀን 2016…
Read More
ኢትዮጵያ ትልቁን ድልድይ በአባይ ወንዝ ላይ ገነባች

ኢትዮጵያ ትልቁን ድልድይ በአባይ ወንዝ ላይ ገነባች

ከስድስት ዓመት በፊት የተጀመረው የአባይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡ በአማራ ክልል ጎንደርን እና ጎጃምን የሚያገናኘው የአባይ ድልድይ በቻይናው ሲሲሲሲ የስራ ተቋራጭ ድርጅት የተገነባ ሲሆን ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወጭ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጀክቱኢንጂነር ለሚ በቀለ አዲሱ የዓባይ ድልድይ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ በአገራችን ከሚገኙ ድልድዮች የተለየ መሆኑን አስታውቋል። ድልድዩ 380 ሜትር ርዝመትና 43 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በአንድ ጊዜም ስድስት መኪኖችን ለማስተላለፍ እንዲያስችል ተደርጎ ተገንብቷል ተብሏል። ድልድዩ በግራና ቀኝ 3 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለው የሳይክል መስመር እንዲሁም 5 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አካቶ እየተሰራ ሲሆን፣ ለከተማዋ እድገትም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በአማራ ክልል…
Read More