Ethiosat

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙንኬሽን ሳተላይት ባለመያዟ ምክንያት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች መሆኗ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል በሚል ነበር መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁት፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጥያቄውን ተቀብሎ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡ ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል በሚል ለቴሌቪዥን ባለንብረቶች ያሳውቃል፡፡ በዚህ መሰረትም 70ዎቹ ስርጭታቸውን በኢትዮሳት በኩል ያደረጉ ሲሆን ዓመታዊ ወጪያቸው ግን እንዳልቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ብሮድካስተሮች ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ወጪ ለመቀነስ ብለው ወደ ኢትዮሳት የገቡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዓመት ለሳተላይት ስርጭት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት…
Read More