14
May
ኦቪድ ግሩፕ እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትን አጠናቀዋል፡፡ ኦቪድ ግሩፕ እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ታሪካዊ በሆነ ትብብር በኮዬ ፈጬ የገነቡትን የቤት ፕሮጀክት አጠናቀው አስረክበዋል፡፡ በ16 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና ዘመናዊ የሆኑ የመኖሪያ ቤት አገልግሎቶችን አሟልተዋል የተባሉት እነዚህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ጥራታቸውን ጠብቀው መገንባታቸው ተገልጿል፡፡ ኮዬ ፈጬ አካባቢ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፤ አራት G+7 እና ሦስት G+9 ሕንጻዎችን፤ በድምሩ ሰባት ሕንጻዎችን የያዘ ሲሆን፤ 120 ባለ ሦስት መኝታ እና 128 ባለ አራት መኝታ፤ በአጠቃላይ 248 የመኖሪያ ቤቶች አሉት። ግንባታው ወደ የትኛውም ሕንጻ የሚያደርሱ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን እና ለምለም አረንጓዴ ቦታዎችን ያካተተ እና የኑሮ ደረጃን ትኩረት አድርጎ፤ ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆን ታስቦ በልዩ…