ኢኮኖሚ

የእስራኤል- ኢራን ጦርነት ለነዳጅ ድጎማ የሚወጣውን ገንዘብ ጨምሮታል ተባለ

የእስራኤል- ኢራን ጦርነት ለነዳጅ ድጎማ የሚወጣውን ገንዘብ ጨምሮታል ተባለ

ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ በየዓመቱ ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ወጪ እንደምታደርግ ተገልጿል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ መጋቢት 2፣ 2018 በሰጡት መግለጫ በእስራኤል-አሜሪካ እና ኢራን መካከል በተጀመረው ጦርነት ምክንያት ለነዳጅ ድጎማ የሚያወጣው ወጪ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ አህመድ ገለጻ ይህ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ኢትዮጵያ አንድ ሊትር ቤንዚን በ129 ብር ለተጠቃሚዎች ስታቀርብ የነበረ ሲሆን ድጎማው ቢቀር ግን የአንድ ሊትር ቤንዚን መሸጫ ዋጋ 157 ብር ይሆን ነበር፡፡ እንዲሁም ነጭ ናፍጣ 129 ነበር በሊትር ሲሸጥ ነበር የተባለ ሲሆን ድጎማው ቢነሳ 182 ነጥብ 8 ብር መሸጥ ነበረበት ተብሏል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ኢትዮጵያ ቤንዚን የ28 ነጥብ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት የ137 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እያስተናገደ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት የ137 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እያስተናገደ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል-ኢራን ጦርነት ምክንያት በሳምንት የ137 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እያስተናገደ መሆኑን ገለጸ ከሰባት ቀናት በፊት የተጀመረው የእስራኤል-ኢራን ጦርነት ጉዳቱ በመላው ዓለም ላይ ሲሆን ኢትዮጵያም የጦርነቱ ተጎጂ ሆኗ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀው በዚህ ጦርነት ምክንያት በየሳምንቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የካርጎ በረራን ሳይጨምር የመንገደኞችን ብቻ 101 በላይ በረራዎችን እየሰረዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በረራዎቹ በመሰረዛቸው ምክንያትም እስከ 137 ሚሊዮን ዶላር በማጣት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ የእስራኤል- ኢራን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀን ወደ ዱባይ ሦስት ጊዜ ፣ ወደ ሻርጃ አንድ ጊዜ፣ ወደ እስራኤል ሦስት ጊዜ፣ ወደ አቡዳቢ፣ ወደ አማን ሁለቴ መንገደኞችን ያመላልስ ነበር። በጦርነቱ ምክንያት አየር መንገዱ በአማካኝ በየዕለቱ 15…
Read More
አንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ወደ 156 ብር ከፍ ማለቱ ተገለጸ

አንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ወደ 156 ብር ከፍ ማለቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባከናወነው 20ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላርን አማካይ በ155 ነጥብ 4 ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ ለገበያ ያቀረበው የውጭ ምንዛሬ መጠን 70 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም፣ ከንግድ ባንኮች በኩል የቀረበው የፍላጎት መጠን ግን 177 ነጥብ 12 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ሆኗል። ይህም አቅርቦቱ ከፍላጎቱ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው ያሳያል። ከፍተኛው የማሸነፊያ ዋጋ 156 ነጥብ 05 ብር ሲሆን ዝቅተኛው የጨረታ ዋጋ ደግሞ 153 ነጥብ 8805 ብር ሆኗል። ባንኩ በዚህ ጨረታ አንድ ዶላርን 155 ነጥብ 88 ብር መሸጡን አስታውቋል። በዚሁ ጨረታ ላይ በአጠቃላይ 20 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ካቀረቡት የዋጋ ተወዳዳሪነት አንጻር 9 ባንኮች ብቻ የቀረበውን የውጭ…
Read More
ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶ ከረንሲን በብር መገበያየትን ከለከለ

ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶ ከረንሲን በብር መገበያየትን ከለከለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ በዲጂታል የንግድ መንገዶች አማካኝነት በብር የሚከናወኑ የሰው-ለሰው (P2P) የገንዘብ ዝውውሮች እና የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይቶች ሕገ-ወጥ መሆናቸውን አስታውቋል። ባንኩ ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በማንኛውም መድረክም ሆነ የልውውጥ ማዕከል በብር የሚደረጉ የዲጂታል ሀብት ግብይቶች ያለ ባንኩ ፈቃድ በፍጹም የተከለከሉ መሆናቸውን አስታውቋል። ይህ እገዳ ማንኛውንም በብር የሚሰላ የክሪፕቶ ከረንሲ ልውውጥን የሚያካትት መሆኑም ተገልጿል። እንደ ብሔራዊ ባንክ ማብራሪያ፣ እነዚህ መድረኮች ለከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ፣ ለገንዘብ ማጭበርበር እና ለውጭ ምንዛሪ ዋጋ መዛባት እጅግ ተጋላጭ ናቸው። በተጨማሪም እንደ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የመሳሰሉ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥርዓቶች በእነዚህ መድረኮች ላይ ባለመኖራቸው ኅብረተሰቡ ለከፍተኛ አደጋ ሊጋለጥ…
Read More
ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው ልማት ባንክ እና አማራ ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ አያሌው በኪሳራ ላይ ላለው ጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሾመዋል። የአማራ ብድርና ቁጠባ ድርጅት በሚል ሲጠራ የነበረው በኋላም ጸደይ ባንክ በሚል ስያሜ የኢትዮጵያን የባንክ ቢዝነስ የተቀላቀለው ጸደይ ባንክ በኪሳራ ላይ ይገኛል። ባንኩ በ2024/25 በጀት ዓመት ብቻ የሁለት ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ከአንድ ወር በፊት ዓመታዊ ጉባኤውን ሲያካሂድ ገልጿል። ይህን ተከትሎም ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የባንኩ አዲስ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተሾሙለት ባንኩ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስታውቋል። በኪሳራ ላይ ያሉ የገንዘብ ድርጅቶችን በመታደግ የሚታወቁት ዶክተር ዮሀንስ ከዚህ በፊት ልማት ባንክን እንዲሁም የአማራ ባንክን ከኪሳራ ወደ ትርፍ መመለሳቸው ይገለጿል። ላለፉት ዓመታት ጸደይ ባንክን በፕሬዝዳንትነት…
Read More
ፓርላማው የሞርጌጅ ባንክ ዳግም እንዲቋቋም ጠየቀ

ፓርላማው የሞርጌጅ ባንክ ዳግም እንዲቋቋም ጠየቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሞርጌጅ ባንክ ወይም የቤት ብድር ባንክን ሀላፊነት ወስዶ መልሶ እንዲያደራጅ ጠይቋል፡፡ በሀገሪቱ ቀድሞ የነበረዉ የሞርጌጅ ባንክ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ንግድ ባንክ መቀላቀሉ ስህተት መሆኑ ተገልጿል። ፓርላመው ይህን የተጠየቀዉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሠረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መሃመድ አብዶ በግምገማዉ ወቅት መንግስት በቤቶች ልማት ላይ ያለውን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት የሞርጌጅ ባንክ መልሶ ማደራጀት አለበት ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዘመናት የቤት ብድር ባንክ ሞርጌጅ እንደነበረና ባልታወቀ ምክንያት ፈርሶ ወደ ንግድ ባንክ የተቀላቀለ መሆኑን የቋሚ…
Read More
ኢትዮጵያ ከጤፍ የተሰራ የወተት ምርትን ለዓለም ገበያ አስተዋወቀች

ኢትዮጵያ ከጤፍ የተሰራ የወተት ምርትን ለዓለም ገበያ አስተዋወቀች

ኦሪጅናል ቴፍ-ሊ የተባለው ከጤፍ የተሰራ የወተት ምርት ዛሬ በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በአምራቾቹ ትብብር በተዘጋጀ የማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከንግድ ማህበረሰቡ፣ ከሚዲያ፣ ከእንስሳት ተዋጽኦዎች ነፃ በሆኑ ምግቦች ምርት እና ግብይት ውስጥ የሚሳተፉ ኢንዱስትሪዎች አባላት እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከእፅዋት የተዘጋጁ የምግብ አማራጮች ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ዝግጅቱ ጤፍን ለአለም አቀፍ ታዳሚዎች የበለጠ ለማስተዋወቅ እድል ፈጥሯል። በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን በመክፈቻ ንግግራቸው ጤፍ በኢትዮጵያዊያን የአመጋገብ ዘይቤ ውስጥ ያለውን ሰፊ ቦታ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚችሉ የምግብ ስርዓቶች ጥናቶች ላይ ሊያበረክት ስለሚችለው አዎንታዊ አስተዋጽኦ አብራርተዋል፡፡ የኦሪጅናል ቴፍ-ሊ (The Original Teff-ly) መስራቾች…
Read More
በኢትዮጵያ ከተሞች ቢስፋፉም የኑሮ ውድነቱ ፈተና መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከተሞች ቢስፋፉም የኑሮ ውድነቱ ፈተና መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በያዝነው የ2026 ዓመት የ6.3 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ ቢተነበይም፣ በአገሪቱ እየታየ ያለው ፈጣን የከተሞች መስፋፋት በመኖሪያ ቤት፣ በመሠረተ ልማትና በመሠረታዊ አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑ ተገልጿል። ይህ ሁኔታ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የከተማ ነዋሪዎች ላይ የኑሮ ውድነትን እያባባሰ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት የከተሞች መስፋፋት የሚታይባት አህጉር ስትሆን፣ የከተማ ነዋሪዎቿ ቁጥር በየዓመቱ ከ3.5 በመቶ በላይ እያደገ ይገኛል። ኢትዮጵያም ለዚህ ፈጣን ዕድገት በምክንያትነት የሚጠቀሱት ከፍተኛ የውልደት መጠን እና ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት ዋነኛ ተዋናይ ናት። ይህ ፍልሰት በመኖሪያ ቤት፣ በመሠረተ ልማትና በመሠረታዊ አገልግሎቶች ላይ ያለውን ፍላጎት በእጅጉ እንዲጨምር አድርጎታል። የፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ደግሞ የቤት ኪራይንና…
Read More
ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

በኢትዮጵያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዛቸውን ገልጿል። የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል። ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም…
Read More
በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሟል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0. ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል። የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአትን ማዘመን እና ለዚያ የሚያበቃ የድጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ባለፈው አንድ አመት…
Read More