05
Sep
ሶስት ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሁዋዌ አዘጋጅነት ለስምንት ቀናት በሚቆይ የዲጂታል ጉብኝት እየተሳተፉ ሲሆን ጉብኝቱ በቻይና ሼንዘን ተጀምሮ ቤጂንግ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ለተመረጡ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ “Huawei Seeds for the Future (SFTF) Tech 4 Good” ያለፈው ዓመት ሰልጣኞች የተዘጋጀው ጉብኝቱ ነሐሴ 26 ተጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3, 2016 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። ጉብኝቱ ለተማሪዎች የቻይናን ዲጂታል መልከዓ ምድር ለመቃኘት፣ የአይሲቲ ክህሎት እና የቴክኖሎጂ ጅምሮችን ለማዳበር፣ እንዲሁም ተማሪዎቹ ስለሚሰሯቸው ስራዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ከኢንዱስትሪ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት እንዲያደርጉ ልዩ እድል ይሰጣል። ተማሪዎች በዚህ ስልጠና እንዲሳተፉ ለማድረግ የማጣራት ሂደትን ያለፉ ሲሆን ከ2023 የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ፕሮግራም ተሳታፊዎች…