11
Jun
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ባህርዳር ያቀኑ ሲሆን ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ይልቃል ከፋለ ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር እንዲሁም ከህብረተሰቡ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል። በዚህ ውይይት ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ " ዋጋ የማይጠይቅ የሠላም አማራጭ ሳለ በፖለቲከኞች የጠብ ርሃብ ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል " ብለዋል፡፡ "ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " ያሉ ሲሆን " አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው " ሲሉም አክለዋል፡፡ "የሁከት እና ግርግር አጀንዳዎች የሚታያቸው ይኖራሉ፤ ነገር ግን ለሕዝብ ካሰብን እና ከሠራን ከሠላም ውጭ የተሻለ…