Coding

ቦይንግ ኩባንያ ከቲንክ ያንግ ጋር በመተባበር ለ60 ኢትዮጵያዊያን ስልጠና ሰጠ

ቦይንግ ኩባንያ ከቲንክ ያንግ ጋር በመተባበር ለ60 ኢትዮጵያዊያን ስልጠና ሰጠ

ለአራት ቀናት የተሰጠው ይህ ስልጠና ከቲንክ ያንግ እና ከአሜሪካው የአቪዬሽን ቦይንግ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው። ስልጠናው ከ20 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ለ60 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ተሰጥቷል። ከሰባት ዓመት በላይ ጀምሮ እድሜ ላላቸው የተሰጠው ይህ ስልጠና ታዳጊዎች ከቴክኖሎጂ ጋር እየተዋወቁ እንዲያድጉ በማሰብ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል። ለታዳጊዎቹ የተሰጠው የስልጠና አይነት ዌብሳይት ማበልጸግ፣ ሮቦቲንግ፣ ኮዲንግ እና አርቲፊሻል እንተለጀንስ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ተቋም ቦይንግ የስልጠናው አካል ሲሆን የበጀት ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል። በቦይንግ ኩባንያ የመካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና ተርኪየ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኩልጅት ጋታ ስልጠናው የቦይንግ ማህበራዊ ሀላፊነት አንዱ አካል ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ መንግሥት ድጅታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የያዘውን እቅድ ለመደገፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥተናል ያሉት"…
Read More
የቲንክ ያንግ ኮዲንግ ስኩል ስልጠና በድጋሜ ሊጀምር እንደሆነ ተገለጸ

የቲንክ ያንግ ኮዲንግ ስኩል ስልጠና በድጋሜ ሊጀምር እንደሆነ ተገለጸ

ቲንክ ያንግ (ThinkYoung) እና ቦይንግ (Boeing) ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 20ኛው የThinYoung Codeing School ምዝገባ መጀመሩን አስታውቀዋል። መርሃ ግብሩ ከሀምሌ 7 እስከ 10 ቀን 2015 ዓ. ም የሚካሄድ ሲሆን እድሜያቸው ከ9-18 ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ነፃ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ትምህርት ይሰጣል ተብሏል። የቲንክ ያንግ ኮዲንግ ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርት በባለሙያዎች የተመቻቹ ሮቦቲክስ እና ሮቦቲከስን  ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን የሚሽፍን ይሆናል። በተጨማሪም የቦይንግ ተወካዮች በአቪዬሽን እና በሌሎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ መስኮች ተነሳሽነትን ለመፍጠር ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች እንደሚያካፍሉ ተገልጿል። እንዲህ ባለው የቲንክ ያንግ እና በቦይንግ አጋርነት በመሰል ኮዲንግ ትምህርት ላይ በተሳተፉ ከ1,300 በላይ ወጣቶች ህይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድረ ሲሆን በቀደሙት ዙሮች ውስጥ…
Read More