29
Mar
ከመልቲቾይዝ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዲኤስቲቪ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች የተለያዩ መዝናኛ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው ፕሮግራም ከዚህ በፊት የነበሩ እና በቀጣይ ስለሚጀመሩ አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራሞቹን አስተዋውቋል፡፡ በመድረኩ ላይ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖፈጣሪ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ቁጥጥር እና ኮርፖሬት ሃላፊ አቶ መታሰቢያ በላይነህ በመድረኩ ላይ እንዳሉት መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ በየጊዜው አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራም እና ይዘቶችን ያቀርባል ብለዋል፡፡ ድርጅቱ በዚህ ወቅት እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ሲያቀርባቸው ከነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪ አዳዲስ ይዘቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡ በድርጅቱ በኩል ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ይቀርቡ ከነበሩት ይዘቶች በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በአማርኛ እና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ይዘቶች…