10
Jul
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። ከተገኘው ገቢ 39.9 በመቶ የድምጽ ፣ 21.7 የኢንተርኔት ፣10.2 የዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ፣ 2.5 ከቴሌብር እና 1.5 ከኢንፍራስትራክቸር እንዲሁም 5 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከዲቫይስ የተገኘ ገቢ መሆነም ተገልጿል ። በበጀት ዓመቱ የኩባንያው የደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ተናግረዋል። ኩባንያው በውጭ ምንዛሬ ገቢ ከሚያገኝባቸው ምንጮች 198 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለውም በ2016 በጀት ዓመት ኢትዮ ቴሌኮም 30…