27
Sep
አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን እስራኤል እና የሊባኖሱ ሂዝቦላህ አዲስ ጦርነት ጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከሚኖሩባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሊባኖስ ዋና ከተማዋ ቤሩትን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በእስራኤል የአየር ላይ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በሊባኖስ የሚኖሩ ከ30 ሸህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከቀሪው የሀገሪቱ ዜጎች ጋር የደህንት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን እንዴት እየመሩ ይሆን ሲል የሀገሪቱ መዲና በሆነችው ቤሩትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ጠይቋል፡፡ ለደህንነቷ በመስጋት ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች አንድ ኢትዮጵያዊ እንዳለችን ከሆነ ነበለት በሚባለው ቦታ ትኖር እንደነበር ነግራናለች፡፡ በአካባቢው ተከታታይ የእስራኤል የአየር ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ ወደ…