09
Mar
የኢትዮጵየ መንግሥት ፌስቡክ እና ዩቲዩብን ጨምሮ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ የጠየቀው ዓለም አቀፉ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነው፡፡ አምነስቲ የማኅበራዊ መገናኛ መድረኮቹ ከተገደቡ አንድ ወር እንደሞላቸው ዛሬ ሐሙስ የካቲት 30፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የአምነስቲ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ፍላቪያ ምዋንጎቪ፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብን ማኅበረሰቡ እንዳይጠቀም ገደብ ከጣሉ አንድ ወር እንደሞላቸው አስታውሰው፤ ይህም ‹‹የዜጎችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና መረጃን የማግኘት መብቶችን በግልጽ የሚጥስ ነው›› ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ አምነስቲ የጠቀሳቸው የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ገደበ የተጣለባቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረ ክስተት ተከትሎ ውጥረት በመስፈኑ ነበር፡፡ የመብቶች ተሟጋቹ በመግለጫው…