ዜና

በሱሉልታ ከተማ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል አሉ።

በሱሉልታ ከተማ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል አሉ።

በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተቋቋመዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ቀርዮ የተሰኘዉ ነዋሪዎች ቤታቸዉ እየፈረሰባቸዉ እንደሆነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤታቸዉ ድንገት ስለሚፈርስባቸዉ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸዉን ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡ ቤቶቹ ያለምን ማስጠንቀቂያ ድንገት በሌሊት ጭምር እየፈረሱ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ “እቃችንን እንኳን ለማንሳት ጊዜ አልተሰጠንም” ብለዋል፡፡ ቤቶቹን ማፍረስ ብቻም ሳይሆን የቤት ክዳን ቆርቆሮና በር ጨምር እየተወሰደበናቸዉ እንደሆነም ሰምተናል፡፡አሁን ላይ ቤት የፈረሰባቸዉ ዜጎች ጊዚያዊ ማረፊያ አጥተዉ ሜዳ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ነዋሪዎቹ ፤ ግማሾቹም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተሰደዱ ነዉ ተብሏል፡፡ “ቤቶቹ ህገወጥ ሆነዉ ቢገኙ እንኳን እንድናፈረስና ለቀን እንድንወጣ ጊዜ መሰጠጥ ነበረበት” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ መንግስት ይድረስልን ሲሉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ…
Read More
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ለቦረና ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር ለግሷል። በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች በድርቅ መጎዳታቸው ሲታወስ ከ3 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳትም ሞተዋል፡፡ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ የዘንድሮን የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው የቦረና ሕዝባችን የ1ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል። በቦረና ዞን ለተከታታይ ለስድስተኛ ጊዜ ዝና ብ አለመዝነቡን ተከትሎ በድርቁ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የዞኑ አስተዳድር አስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር 100 ሚሊዮን ብር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ ሲያደርግ ሌሎችም የመንግስት እና የግል ተቋማትም ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ በኢትዮጵያ…
Read More