06
Mar
ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገር ልትልክ ነው በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገራት በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሥራ ለመላክ በመንግሥት እቅድ መያዙ ተገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም በአማራ ክልል ኹሉም ዞኖች ሰሞኑን ወደ አረብ አገር ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ወጣት ሴቶች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ኢትዮ ነጋሪ ሰምታለች፡፡ ለአብነትም በምስራቅ ጎጃም ዞን ሦስት የስልጠና ማዕከላት የተዘጋጁ ሲሆን፣ በሞጣ፣ ደብረ ማርቆስ እና ደጀን ከተሞች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች የቤት አያያዝና ሌሎች አስፈላጊ የሥራ ስልጠናዎች እንደሚሰጡኢትዮ ነጋሪ ከዞኑ መረጃ አግኝታለች፡፡ ስልጠናው ለ20 ቀን በመንግሥት በነጻ የሚሰጥ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ከስልጠናው በኋላ ፈቃደኛ የሆኑ ሴቶች ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚያቀኑበት የዚህ…