EthiopiaAI

የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና መኮንኖች ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና መኮንኖች ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦር አመራር መኮንኖች በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል። ኤርትራ ወታደራዊ ልኡክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዓቅም እና እየተከናወኑ ያሉ የምርምር እና ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፤ ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ባሉ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ዙሪያ ለቡድኑ አባላት ገለጻ ማድረጋቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡ የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦሩ አመራሮች ቡድን አስተባባሪ ጀነራል አብርሃ ካሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ያደረጉት ጉብኝት ለአገራቸው ብዙ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን መናገራቸው ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቴክኖሎጂው ዘርፍም አብረው መስራት የሚያስችላቸው እድል ስለመኖሩም የተገነዘቡበት ጉብኝት መሆኑን መጠቆማቸውም ተመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመት በፊት ወደ ደም አፋሳሽ…
Read More