01
Apr
የፌደራል መንግስት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መልቀቅ እንደሚጀምር የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል። ለክልሉ የሚለቀቀው በጀት፤ ለሌሎች ክልሎች እንደሚደረገው ሁሉ በወራት ተከፋፍሎ የሚላክ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። የፌደራል መንግስት ለትግራይ በጀት ለማስተላለፍ ከስምምነት ላይ መድረሱን በተመለከተ አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ተናግረው ነበር። ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተሾሙት አቶ ጌታቸው፤ የፌደራል መንግስት በጀት መፍቀዱን፤ ሆኖም የገንዘብ መጠኑን በተመለከተ ግን “ገና እንነጋገራለን” ማለታቸው ይታወሳል። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው በበኩላቸው፤ የትግራይ ክልል በጀት “የሚታወቅ” መሆኑን ገልጸዋል። የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እስኪቋቋም የበጀት ድጎማ ሳይለቅቅ ቢቆይም፤ በክልሉ ውስጥ…