02
Apr
ከመልቲቾይዝ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዲኤስቲቪ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች የተለያዩ መዝናኛ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የይዘት ቀንን በአዲስ አበባ ያከበረ ሲሆን በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ብዙሃን መገኛኛ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡ ድርጅቱ በዚህ ወቅት እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ሲያቀርባቸው ከነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪ አዳዲስ ይዘቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡ በድርጅቱ በኩል ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ይቀርቡ ከነበሩት ይዘቶች በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በአማርኛ እና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ይዘቶችን በቅርቡ እጀምራለሁም ብሏል፡፡ ዲኤስቲቪ አሁን ላይ በአቦል ቲቪ እና አቦል ዱካ ፕሮግራሙ አደይ፣ ደራሽ፣ አስኳላ፣ ሶረኔ፣ አጋሮቹ፣ ገብርዬ እና ሌሎችንም መዝናኛዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ የመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ገሊላ ገብረሚካኤል በፕሮግራሙ ላይ…