14
Apr
የኢትዮጵያ ብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ማህበር በጋዜጠኞች እስር ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። ማህበሩ እንዳለው ብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ደግሞ በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳለባቸው እና የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት እንደሚያምን ገልጿል። ይሁንን " ከለውጡ በኋላ " በሀገራችን የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት እንዲረጋገጥ ማህበራችን ብዙ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየተሸማቀቁ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቁሟል። የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ አራጋው ሲሳይ ፣ ገነት አስማማው ፣ ጌትነት አሻግሬ ፣ በየነ ወልዴና ቴዎድሮስ አስፋው…