20
Apr
በአዲስ አበባ ከአዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ እንጦጦ መስመር ላይ የተገነባው፤ "ስቴይ ኢዚ ፕላስ" ሆቴል ከኹለት ሳምንታት በኋላ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አሚር ሰኢድ እንዳሉት ሆቴሉ በጥንዶቹ ዳግማዊ መኮንን እና ህይወት አየለ ባለቤትነት የተገነባ ሲሆን ሆቴሉ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል ብለዋል፡፡ በአምስት ዓመት ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ታስቦ ግንባታው የተጀመረው ይህ ባለ ስምንት ወለል ህንጻ ኮሮና ቫይራ ተጨምሮበት በስምንት ዓመት ውስጥ መጠናቀቁን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ሆቴሉ በባለ አምሰት ኮከብ ደረጃ መገንባቱን የተናገሩት ደግሞ የሆቴሉ ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሂወት አየለ ናቸው፡፡ እንደ ወይዘሮ ሂወት ገለጻ ሆቴሉ በአጠቃላይ 103 ክፍሎች፣ ከ15 እስከ 1 ሺሕ…