ዜና

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው ኤሌክትሪክ ከ118 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው ኤሌክትሪክ ከ118 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 118 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የኤሌክትሪክ ሃይል ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይም ኢትዮጵያ ለኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳንና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል እየሸጠች እንደምትገኝ አብራርተዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመት 25 ሺሕ በላይ ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ 29 ሺሕ በላይ ጊጋ ዋት ሰዓት ማመንጨት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ከተመረተው ኃይል ውስጥም ለኬንያ 85 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ለማከናወን ታቅዶ 86 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡ እንዲሁም ለጅቡቲና ሱዳን ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ28 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ28 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገለጸ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በተቋሙ የበጀት አመት አፈጻጸም ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ጥያቄዎች ተነስተውላቸው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከነዚህም ጥያቄዎች መካከል ከበረራ ትኬቶች ውድነት ጋር እና አየር መንገዱ በኤርትራ ከተያዘበት ገንዘብ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ሲሆን ዋና ስራ አስፈጻሚው ምላሽ ሰጥተውበታል። ከሀገር ውስጥ በረራ ጋር በተያያዘ የ28 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። "የዓለም አቀፍ በረራዎች ትኬት ኮምፒውተር ውስጥ በዶላር ነው የተጻፈው ሰው ትኬት ሲገዛ በእለታዊ የዶላር ምንዛሬ ተመን ነው ይህንን ምንም ልናደርግ አንችልም። የሃገር ውስጥ በረራ ግን በብር ነው የተጻፈው ባለፈው አመት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወቅት አልጨመርንም የዶላር…
Read More
በኢትዮጵያ በህይወት የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ መግባቱን ኢሰመኮ ገለጸ

በኢትዮጵያ በህይወት የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ መግባቱን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ ክልል ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ከተጠናቀቀ ዓመት ቢያልፈውም  ህገ ወጥ እና የተራዘመ እስር እንደቀጠለ ነው ተባለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳለው ከአማራ ክልል በተጨማሪ በኦሮሚያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያም በወቅታዊ ሁኔታ በሚል ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ አሁንም እየታሰሩ ነው፡፡ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ በየፖሊስ ጣቢያው በተራዘመ እስር ላይ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን ኮሚሽነሩ ብርሃኑ አዴሎ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሌለበት ሁኔታ በወቅታዊ ሁኔታ እያሉ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን መፈፀምም ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በቀጠለው የትጥቅ ግጭት የሰላማዊ ሰዎች በሕይወት የመኖር መብታቸው እየተጣሰ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ለአካላዊ ጉዳት የሚዳረጉ እና ለተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የ10 በመቶ ታሪፍ አጸናች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የ10 በመቶ ታሪፍ አጸናች

በተሻሻለው የትራምፕ ታሪፍ ኢትዮጵያ  ቀድሞ በተጣለባት ዝቅተኛው 10 ፐርሰንት ታሪፍ እንድትቀጥል ተደርጓል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአሥርተ ዓመታት የቆዩትን የዓለም ንግድ አሠራሮች ለመለወጥ በሚያደርጉት ጥረት ከሰባ በላይ አገራት ላይ አዲስና የተቀየረ የንግድ ቀረጥ ተግባራዊ ሊያደርጉ መሆኑን አስታወቀዋል። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የተጣለባትን የ10 በመቶ ታሪፍ የተቀበለች ሲሆን ታሪፉ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንደሚያሳድግላት አስታውቃለች። ትናንት በተፈረመው የአስፈጻሚ ትዕዛዝ መሰረት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገሪቱን የንግድ ጉድለት ከዋነኛ አጋሮች ጋር ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ ነው በማለት የገለፁ ሲሆን፣ በዚህም እስከ 41 በመቶ የሚደርስ አዲስ የገቢ ምርቶች ላይ የሚጣል ታሪፍን ተፈፃሚ አድርገዋል። በካናዳ ምርቶች ላይ የተጣለው የንግድ ቀረጥ ወደ 35 በመቶ ከፍ ማለቱ ቀድሞውንም የተወጠረው የንግድ ግንኙነት ይበልጥ…
Read More
ኢትዮጵያ የእብድ ውሻ በሽታ ከተስፋፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት ተባለ

ኢትዮጵያ የእብድ ውሻ በሽታ ከተስፋፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት ተባለ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአለም አቀፍ ደረጃ በውሻ እብደት በሽታ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ህንድ ቀዳሚውን ቦታ ስትይዝ ከአፍሪካ ደግሞ ኢትዮጵያ እንደሆነች የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዝግጁነት እና የአቅም ግንባታ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደባልቄ አባተ እንዳሉት የውሻ እብደት በሽታ አሁን ላይ በሀገራችን እየተስፋፋ እየመጣ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን በዛ ልክ ትኩረት እየተሰጠው እንዳልሆነ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ  4900 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነክሰው የመጡ ሲሆን ምልክት ሳያሳዩ ክትባት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል:: ከነዚህ መካከል 1 በመቶ ያህሉ ህክምናውን እንዳቆሙ ገልፀዋል:: ከዚህ በፊት የእብድ ውሻ ክትባት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቦታዎች 13 የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ 23 መድረሳቸውን…
Read More
ሕንዳዊው በኦሮሚያ ክልል አዳማ አካባቢ ህይወታቸው አልፎ ተገኙ

ሕንዳዊው በኦሮሚያ ክልል አዳማ አካባቢ ህይወታቸው አልፎ ተገኙ

ህንዳዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ መገኘቱን በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ አስታውቋል። ህንዳዊ ዜግነት ያለው እና በአዳማ አከባቢ ቢሮውን ባደረገው በካልፓታሩ ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተሰኘ ተቋም (KPIL) ሲሰራ የነበረ ግለሰብ በአዳማ አከባቢ ሞቶ መገኘቱን በኢትዮጵያ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲ አስታውቋል። ኤምባሲው ባወጣው አጭር መግለጫ ናቭ ሱቫሪዮ የተሰኙትና በአዳማ-አዋሽ ፈጣን መንገድ ፕሮጀክት ላይ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ግለሰብ፥ " አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ የተገኘ ሲሆን የሞቱን ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው " ሲል አስታውቋል። ሕንዳዊው አሟሟታቸው እስካሁን በይፋ ያልተገለጸ ሲሆን ተገድለው ይሁን በህመም እንደሞቱ ምርመራው እንደቀጠለ ነው ተብሏል። የኦሮሚያ ክልልም ሆነ የጌደራል ፖሊስ እስካሁን ስለ ሕንዳዊው አሟሟት መረጃ ከመስጠት…
Read More
ቱርክ የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አጋር ሆነች

ቱርክ የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አጋር ሆነች

የኢትዮጵያና የቱርክ የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነትን የሚያጠናከር የቢዝነስ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በቱርኩ የአለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም/ World Cooperation of Industries Forum-WCI Forum/ / እና በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አማካኝነት የተሰናዳው ስምንተኛው የ ደብሊው ሲአይ / WCI የቢዝነስ ፎረም ዛሬ ተጀምሯል፡ ፡ በንግድ ፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር  ዘለቀ ተመስገን፤ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ ፕሬዚዳንት  ዘሀራ መሀመድ፤ የዲፕሎማቲክ እና የንግዱ ማህበረሰብ እና  ሌሎች ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡ ፡ በመድረኩ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሀፊ መሰረት ሞላ የኢትዮጵያ እና የቱርክ አመታዊ የንግድ ልውውጥ መጠን እ.አ.አ በ2023 ከ…
Read More
ሻኩራ ፕሮዳክሽን የቻይና አምባሳደር ከተሰኘው ተቋም ጋር ስምምነት ፈጸመ

ሻኩራ ፕሮዳክሽን የቻይና አምባሳደር ከተሰኘው ተቋም ጋር ስምምነት ፈጸመ

በካሙዙ ካሳ የተቋቋመው ሻኩራ ፕሮዳክሽን የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ ከቻይና አምባሳደር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። በቤጂንግ ከተማ የተፈረመው ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ ወደ ቤጂንግ ያቀናው "ኢትዮ ኪን" ባህል ቡድን አንድ አካል ነው። በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት የኢትዮጵያን እና ቻይናን ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ትምህርት እና ሌሎች የመልካም ገጽታ ማስተዋወቅ ስራዎችን በጋራ ይሰራሉ ተብሏል። የቻይናው የባህል እና ሚዲያ አገናኝ ኩባንያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሚንግዙ ዛንግ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት "የአባይ ወንዝ መገኛ፣ ቡና መገኛ፣ ታላቅ ህዝብ እና ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ባህል ለማስተዋወቅ እንፈልጋለን" ብለዋል። "የቻይና ባህል ባለፈው ታሪክ ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከፈጠራ ጋርም እንደሚያያዝ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም በቀጣይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ…
Read More
ኢትዮጵያ በአሜሪካ ታሪፍ ምክንያት አማራጭ የቡና መዳረሻ እየፈለገች መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ በአሜሪካ ታሪፍ ምክንያት አማራጭ የቡና መዳረሻ እየፈለገች መሆኗን ገለጸች

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ የዓለማችን ሀገራት ላይ አዲስ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል። አዲሱ ታሪፍ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው ጠቅላላ ምርት ላይ የ35 በመቶ ገቢ እንዲቀንስ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር የአሜሪካ አስተዳደር ፖሊሲ ከሀገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ 35 በመቶ የሚሆነውን የሚነካ ነው ብለዋል። በዚህ ምክንያትም ከአሜሪካ ባለፈ አማራጭ የውጭ ገበያዎችን በመመልከት ላይ መሆናቸውንም ሻፊ ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያን ቡና ወደ ሩቅ ምስራቅ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የማስፋት እቅድ ተይዟል ተብሏል። በተያዘው በጀት ዓመት ውስጥም 20 አዳዲስ የቡና ወጪ ንግድ መዳረሻዎችን የመክፈት እቅድ እንደተያዘም ተገልጿል። እንዲሁም ዋነኛ የኢትዮጵያ ቡና ገዢ ወደ ሆኑት ቻይና፣ ጃፓን፣…
Read More
ሴኔጋላዊው አል ሀጂ ዲዮፍ የዋናው ስፖርት ኩባንያ አምባሳደር ሆነ

ሴኔጋላዊው አል ሀጂ ዲዮፍ የዋናው ስፖርት ኩባንያ አምባሳደር ሆነ

የሴኔጋሉ የእግር ኳስ ኮኮብ አልሀጂ ዲዩፍ በኢትዮጵያ ላለ አንድ የስፖርት ትጥቅ አልባሳት አምራች ኩባንያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን "ከአፍሪካ ምርጡ ትጥቅ አምራች ጋር ስምምነት ፈፅሜያለሁ “ ብሏል ዲዩፍ። ሴኔጋላዊው የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ኤል ሀጂ ዲዩፍ የኢትዮጵያው ትጥቅ አምራች ብራንድ ዋናው አምባሳደር በመሆን መሾሙን ኩባንያው ገልጿል። ታሪካዊው ተጫዋች የዋናው ስፖርት አልባሳት በሚመረትበት አዲስ አበባ ሀብቴ ጋርመንት እና ህትመትን ከጎበኘ በኋላ ስምምነት ፈፅሟል። “ ከአፍሪካ ምርጡ ትጥቅ አምራች ጋር ስምምነት ፈፅሜያለሁ “ ሲል ዲዩፍ ከጉብኝቱ በኋላ ተናግሯል። አክሎም  "በቀጣይ ከትልልቅ ታሪካዊ ተጫዋቾች ጄጄ ኦኮቻ ፣ ኑዋንኩ ካኑ ፣ አዲባየር እና ካሊዱ ፋዲጋን በማምጣት ዋናውን በአለም ገናነቱን እናሳየለን "…
Read More