22
Aug
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ በተከሰተው ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር ምንክንያት ወደ ሌላ አየር ማረፊያዎች እያዘዋወረ መሆኑን አስታወቀ በአዲስ አበባ በተከሰተዉ ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር አብዛኛው በረራዎች ቦሌ አዉሮፕላን ማረፊያ ሊያርፍ ባለመቻሉ ምክንያት ወደ ሌላ አየር ማረፊያዎች እንዲቀየሩ መደረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል ። አየር መንገዱ እንደገለፀው ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ባለዉ ከፍተኛ ጭጋግ ( ጉም) ምክንያት የአየር ማረፊያዎችን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወረ መሆኑን እና ይህም በሀገር ዉስጥ እና በአለም አቀፍ በረራዎች ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ብሏል። በተጓዦች ላይ ለደረሰዉ መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ በተጓዦች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ መጉላላቶችን ለመቀነስ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ጣቢያ…