መነሻ ገፅ

ኢትዮጵያ ወደ አግዋ የመመለስ እድል አላት?

ኢትዮጵያ ወደ አግዋ የመመለስ እድል አላት?

በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ነበር አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአሜሪካ የንግድ ችሮታ (አግዋ) እድል ያገደችው። የእግዱ ዋነኛ ምክንያትም በጦርነቱ ምክንያት በዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ነው የሚል ሲሆን ኢትዮጵያ የአሜሪካንን ውሳኔ ተቃውማም ነበር። የአግዋ እድል መሰረዝ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ባሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የተቀጠሩ ዜጎችን ስራ አጥ በማድረግ በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያንን ይጎዳል ስትል ኢትዮጵያ አሜሪካ ውሳኔዋን እንድታጤነው ጠይቃም ነበር። ይሁንና ዋሸንግተን ኢትዮጵያን ከአግዋ እግድ እስካሁን ያላነሳች ሲሆን የመነሳት እድል ይኖራት ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ጥያቄው በተለይም የጦርነቱ ዋነኛ ተሳታፊዎች የሆኑት የፌደራል መንግሥት እና ህወሀት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች። ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል። አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡ ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል መሆኑን ገልፀዋል። ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ ያስችላል ተብላል።
Read More
ኢትዮጵያዊው አበበ ቢቂላን ለማሰብ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሊሮጥ መሆኑን አስታወቀ

ኢትዮጵያዊው አበበ ቢቂላን ለማሰብ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሊሮጥ መሆኑን አስታወቀ

የፊታችን እሁድ መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም የ2023 የሮም ማራቶን ይካሄዳል። በዚህም ማራቶን ታሪክ ራሱን ይደግማል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያዊው የባዶ እግር ሯጭ እንዲሁም ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ቁልፍ ዳይሬክተር በመሆን የሰራው የ45 ዓመቱ ኤርሚያስ አየለ ሙሉ ማራቶን በባዶ እግሩ ይሮጣል። ኤርሚያስ አየለ ይህንን የሚያደርገው ለኢትዮጵያው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ክብር እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ሲል ነው። " አበበ ቢቂላ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት የመጀመሪያው ጥቁር በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአፍራካውያን ስኬት መሰረት ጥሏል " የሚለው ኤርሚያስ " ሆኖም ግን ለሰራው ታሪክ የሚገባውን ያህል እውቅና እንዳላገኘ ይሰማኝ ነበር " ብሏል። ኤርሚያስ ፤ የአትሌት አበበ ቢቃላ ታሪክ ሁሌም…
Read More
ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን ምርጫ ቦርድ አወገዘ

ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን ምርጫ ቦርድ አወገዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከሉን አወገዘ። ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዳያካሂዱ የተከለከሉትን ፓርቲዎች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ቦርዱ በመግለጫው ፓርቲዎች ጉባዔ እንዳያካሄዱ የከለከሉት እነማን እንደሆኑ እንዳላወቃቸው ገልጾ ነገር ግን እገዳውን የጣሉት አካላት የህግ አስፈፃሚ ሃላፊዎች ትእዛዝ እንደሆኑ አስታውቋል። እናት ፓርቲ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲና አዲስ የተመሰረተው ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ (ጎጎት) ፓርቲዎች ባሳለፍነው ሳምንት የፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ በጸጥታ አካላት መከልከላቸውን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል። በመግለጫውም በፓርቲዎቹ ላይ የደረሰው ወከባ ከህግ አንፃር ትክክል አለመሆኑን ገልፀው ፤በቀጣይም ይህን ችግር የፈጠሩ አካላትን አጣርቶ ማቅረብ የፍትህ አካላት ስራ እንደሆነ ገልቷል። አዲስ የተመሰረተው የጎጎት ፓርቲ አመራሮችም መታሰራቸውን የተናገሩት የምርጫ…
Read More
በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙ ጳጳሳት አህጉረ ስብከቶችን መልቀቃቸው ተገለጸ

በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙ ጳጳሳት አህጉረ ስብከቶችን መልቀቃቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አገረ ስብከት በሦስት አባቶች ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ በሆነ መልኩ ለ25 አባቶች ሕገ ወጥ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት መሰጠቱ አይዘነጋም፡፡ ይህን ተከትሎም ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 18 ቀን 2015 በጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባዔ፣ እነዚህን አካላት ከቤተክርስቲያን ሕብረት ለይቶ ማውገዙ፣ እንዲሁም በየትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ እንዳይገኙ የእግድ ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ ችግሩ በእርቅ ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኩል በተደረገው ስምምነት መሰረት፣ በሹመቱ የተካተቱ አካላት ወደ ቀድሞ ሥማቸው እንዲመለሱ ስምምነት ከተደረገ በኋላም፤ ጉዳዩ በስምምነቱ መሰረት አለመፈጸሙን ቤተክርሰውቲያኗ በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡ ሕገ ወጥ የተባሉት ተሹዋሚዎች ከስምምነቱና ከሲኖዶስ ውሳኔ አፈንግጠው፣ ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በተለይም በወለጋ…
Read More
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ገቡ

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ገቡ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ጀምረዋል። አንቶኒ ብሊንከን በአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ኢትዮጵያን እና ኒጀርን እንደሚጎበኙ ተገልጿል። ሚንስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፈጸጸም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ፣ ከሲቪል ሶሳይቲ እና የፖለቲካ አመራሮች ጋር እንደሚመክሩም ይጠበቃል። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ግንኙነታቸው ሻክሮ የቆዩት ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ህዳር በዋሽንግተን በተካሄደው የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ኤርቪን ጆሴፍ ማሲንጋን በኢትዮጵያ የአሜሪካ…
Read More
በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ የኢትዮጵያዊያን ባህል ለማስተዋወቅ ዋና ዓላማው ያደረገ የኢትዮጵያ ቡቡና አፈላል ሂደትን እና ተያያዥ ባህልን የሚያሳይ አውደ ርዕይ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል። በዋርካ ኮፊ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ አውደ ርዕይ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ይዘጋጃል ተብሏል። የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ በአውደ ርዕዩ ዝግጅት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ "በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ቡና አቆላል፣ አጠጣጥ እና ተያያዥ ባህሎች ለታዳሚያን ይቀርባል" ብልዋል። በዝግጅቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መጋበዙን የሚናገሩት ወይዘሮ ሰዓዳ የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት የሚታወቁ ሀገራት አምባሳደሮች እና ሌሎችም በእንግድነት እንደሚገኙም ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ባህልና…
Read More
መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል መባሉን አስተባበለ

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል መባሉን አስተባበለ

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀበሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ምክንያት የመማር ማስተማር ሥራው የተቋረጠው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሥራውን እንደሚጀምር በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘገብ ቆይቷል። በዚህም ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥሉት አራት ወራት 24 ሺሕ የሚጠጉ የቀድሞ ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ እና ከመስከረም ወር 2016 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለጸ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በመንግሥት በኩል የሚያስፈልግ በጀት ሁሉ እንደተለቀቀለትም ተነግሯል። ነገር ግን ይህ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች እና አመራሮች አረጋግጠዋል። መቐለ ዩኒቨርሲቲም ይህንን ዜና የሚመለት መረጃ በይፋዊ የፌስቡክ እና የትዊተር አካውንቱ ላይ አላወጣም። የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሓጎስ ዩኒቨርሲቲው ሥራ ለመጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር…
Read More
መንግሥት ለአዲስ አበባ አመራሮቹ ለሞባይል ስልክ 140 ሺህ ብር ፈቀደ

መንግሥት ለአዲስ አበባ አመራሮቹ ለሞባይል ስልክ 140 ሺህ ብር ፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮች የእጅ ስልክ መግዣ 140 ሺህ ብር ድረስ ፈቀደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በጥር ወር ላይ በወሰነዉ ዉሳኔ መሰረት፣ ለከተማዋ አመራሮች የሞባይል ስልክ ቀፎ ግዢ መፍቀዱ ተገልጿል። በዚህም መሰረት ለከንቲባ እና ለከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ 140 ሺህ ብር ተመድቧል። ለምክትል ከንቲባ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ደረጃ ለተሿሙ አመራሮች እና ለምክትል አፈ-ጉባኤ ስልክ መግዣ 120 ሺህ ብር መወሰኑንም ሰምተናል ሲል ኢትዮ ኤፍ ዘግባል። ለክፍለ ከተማ 50 ሺህ ፣ለወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ የ40 ሺህ እንዲሁም ለወረዳ ቀሪ አመራሮች 30 ሺህ ብር የሚያወጣ የሞባይል ስልክ እንዲገዛላቸዉ ተፈቅዷል። ይህንን የሚያስፈፅም ደብዳቤም በየክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች ጭምር እንደተበተነ ተገልጿል።
Read More
<strong>ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ</strong>

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

በሳሙኤል አባተ ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገልጻል። ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል። አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል። ኢንተርኔት ከተዘጋ አንድ ወር ያለፈ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የኢትዮጵያ መንግሥት ኢንተርኔት እንዲከፍት ጠይቀዋል። በአሁኑ ወቅት የኢንተርኔት ገደብ የተደረገባቸው ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ  ገደብ የተደረገባቸው የትስስር ገጾች ናቸው። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊትም የኢንተርኔት ገደብ በመጣል የምትታወቅ ሲሆን በተለይም…
Read More