Blog

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ሊሰበሰብ ነው

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ሊሰበሰብ ነው

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያና ሶማሊያ ጉዳይ ላይ ሊሰበሰብ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱን ተከትሎም ሶማሊላንድ የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ሶማሊያ የዲፕሎማሲ የበላይነት ለማግኘት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። በዚሁ መሰረት ሶማሊያ ባለፈው ሳምንት  ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት የተመድን ቻርተር ጥሷል በሚል ምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲቀመጥ እና እንዲወያይበት አመልክታም ነበር። ይህንን ተከትሎም የጸጥታው ምክር ቤት የወሩ ፕሬዝዳንት ፈረንሳይ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት አጀንዳ ስር ለመምከር ስብሰባ መጥራቷ ታውቋል። የጸጥታው ምክር ቤት በዛሬው…
Read More
በአዲስ አበባ በእስረኛ ምግብ ውስጥ ካናቢስ የተሰኘው አደገኛ ዕጽ ተያዘ

በአዲስ አበባ በእስረኛ ምግብ ውስጥ ካናቢስ የተሰኘው አደገኛ ዕጽ ተያዘ

በምግብ ውስጥ  አደንዛዥ ዕፅ  ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ ከናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዞ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ የሄደው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነበር፡፡ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ ምግብ ይዞለት የሄደው ይኸው ተጠርጣሪ ከድፍረትም ድፍረት የሚያሰኝ ተግባር ነበር የፈፀመው፡፡ በወቅቱ በሳህን የተቋጠረው ምግብ እንጀራ ፍርፍር በማካሮኒ ነበር፡፡  በእነዚያ የማካሮኒ ቀዳዳዎች ውስጥ የሚያብለጨልጩ ነገሮች ተወታትፈዋል፡፡ ምግቡን ፈትሸው የሚያስገቡት የፖሊስ አባላት ባዩት ነገር ተጠራጥረዋል፤ ምግቡ ተዘርግፎ ሲፈተሽ ብዛት 51 የማካሮኒ ፍሬዎች በተጠቀለሉ የአልሙኒየም ወረቀቶች  አባብጠዋል፡፡ ወረቀቶቹን በመፍታት ለማየት ሲሞከርም ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ ሆኖ…
Read More
አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣን ለቀቁ

አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣን ለቀቁ

የኢትዮጵያ ገዢ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣናቸው ለቀቁ፡፡  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሸኘታቸውን ፓርቲያቸው አስታውቋል። የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ " የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል አቶ ደመቀን በክብር ተሸኝተዋል " ሲል ገልጿል። አቶ ደመቀን መኮንንን በመተካት የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። አቶ ደመቀ ከፓርቲው አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች መሆኑ ተነግሯል። አቶ ደመቀ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና…
Read More
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አፍሪካ እንደሚመጡ ተገልጻል። እንደ ብራዚል ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ አዲስ አዲስ አበባ ይመጣሉ። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ ከአዲስ አበባ በተጨማሪም በግብጽ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል። ከአፍሪካ በመቀጠል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቁር ህዝቦች የሚኖሩባት ብራዚል ከአፍሪካ ጋር የሚያስተሳስራት ብዙ ታሪክ አላት። ፕሬዝዳንቱ ዳ ሲልቫ ስለ ጉብኝታቸው እንዳሉት "ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያለባትን የታሪክ እዳ መክፈል ትፈልጋለች" ብለዋል። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ የሚጓዙት ፕሬዝዳንት ሲልቫ ከዚህ በፊት በአንጎላ፣ ኬፕ ቩርዴ እንዲሁም በሳኦቶሜ…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት  11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት  11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወይዘሪት ፍሬህይወት የ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ ተቋሙ በስድስት ወሩ በመላው ሀገሪቱ 232 አዳዲስ የሞባይል  ኔትወርክ ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ተጨማሪ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን  አዲስ የሞባይል  ኔትወርክ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል መሰረተ ልማት መገንባቱን የገለጸ ሲሆን የድርጅቱ አጠቃይ ደንበኞች ቁጥርም 81 ሚሊዮን እንደደረሱ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በግማሽ ዓመቱ ውስጥ በገጠራማ የሀገሪቱ አካባቢዎች 41 አዲስ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋልም ተብሏል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም ደንበኞች ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛው ተቋም ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ለገባው ሳፋሪኮም የቴሌኮም ኩባንያ ጋር ብርቱ ፉክክር እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ ድርጅቱ ባለፉት…
Read More
በኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት 21 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መዘግየታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት 21 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መዘግየታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለመስራት ካቀዳቸዉ 54 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ዉስጥ 21 ያህሉን በጸጥታ ችግር መተግበር እንዳልቻለ አስታወቀ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን የ 2016 አመት ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  አቅርበዋል። አስተዳደሩ በወራቱ ለማከወን ካከቀዳቸዉ 54 ፕሮጀክቶች ዉስጥ 21 ያህሉን በጸጥታ ችግር መተግበር እንዳልቻለ ዋና ዳይሬክተሩ ለቋሚ ኮሚቴዉ ተናግረዋል። በዚህም በስድስቱ ወራት የነበረዉ የዲዛይን ስራዎች አፈጻጸም 57 በመቶ ሲሆን ይህም ዝቅተኛ እንዲሆን እንዳደረገበት ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። በተጨማሪም በዉጭ አማካሪ ድርጅት ለተሰራ ስራ ክፍያ የዉጭ ምንዛሪ በመዘግየቱ የተጓተቱ ፕሮጀክቶች መኖራቸዉንም ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል። በተለያዩ ምክኒያቶችም 84 ፕሮጀክቶች መቋረጣቸዉ እና ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ዉላቸዉ መሰረዙንም…
Read More
የዓለም ገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባኤ በኡጋንዳ እየተካሄደ ነው

የዓለም ገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባኤ በኡጋንዳ እየተካሄደ ነው

የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ወይም በምህጻረ ቃሉ ናም በመባል የሚታወቀው ይህ ተቋም በፈረንጆቹ 1961 ላይ የተቋቋመ ሲሆን ዓለምን ከቀዝቃው ጦርነት ድባቴ ማውጣት ደግሞ ለድርጅቱ መመስረት ዋነኛ ምክንያት ነበር፡፡ 120 ሀገራትን በአባልነት የያዘው ይህ ንቅናቄ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎችን በጋራ መታገል፣ ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎችን መደገፍ እና የነጻ ሀገር ምስረታን ማበረታታትም ሌላኛው ዓላማውም ነው፡፡ ከመንግስታቱ ድርጅት በመቀጠል በርካታ ሀገራትን በአባልነት የያዘው ይህ ንቅናቄ ዋና መቀመጫውን ምስራቅ አውሮፓዊቷ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አሁን ደግሞ የሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ አድርጎ ተመስርቷል፡፡ ድርጅቱ እንዲመሰረትም የቀድሞው የዩጎዝላቪያ ፕሬዝዳንት  ጆሴፍ ቲቶ፣ የሕንዱ ጃዋህራል ኔህሩ፣ የግብጹ ገማል ናስር፣ የጋናው ክዋሜ ንኩሩማህ እና የኢንዶኔዢያው ሱካርኖ ዋና መስራች መሪዎች እና ሀገራት…
Read More
የአፍሪካ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ያስወጣቸውን ሰራተኞች እንደሚመልስ ገለጸ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ያስወጣቸውን ሰራተኞች እንደሚመልስ ገለጸ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ከሁለት ወር በፊት በአዲስ አበባ ያሉ ሁለት የባንኩ ሰራተኞች በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ድብደባ፣ እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውቆ ነበር። ባንኩ እንዳለው ሁለት ሰራተኞቹ የቬና የዲልሎማሲ ጥበቃ ስምምነትን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሮ አስተናጋጅ ሀገራት ስምምነትን የጣሰ ክስተት በኢትዮጵያ መፈጸሙንም ገልጿል። የተፈጠረውን ክስተት ለኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ማመልከቱን የሚገልጸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጉዳዩ መፈጸም እንደሌለበት፣ ህግ መጣሱን እና ጉዳዩ ተመርምሮ እርምጃ እንደሚወሰድ በኢትዮጵያ በኩል ቃል ተገብቶልኛል ሲልም በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡ ባንኩ አሁን ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል በገባው መሰረት በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዳልወሰደ እና ጉዳዩ ስለመመርመሩ መረጃ እንዳልሰጠው ገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎም ባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እና…
Read More
ሶማሊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በግዛቷ እንዳያርፍ ከለከለች፡፡

ሶማሊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በግዛቷ እንዳያርፍ ከለከለች፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና በራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከሶስት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ 20 ኪሎሜትሮች የሚረዝም የባህር ጠረፍ እንድትከራይ እና በምትኩ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድትሰጥ የሚያስችል ነው። ይህ ስምምነት ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበረራ ቁጥሩ ET8372 የተሰኘ አውሮፕላን ወደ ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በዛሬው ዕለት በረራ በማድረግ ላይ እያለ እንዲመለስ መደረጉ ተገልጿል፡፡ የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በቀድሞ ስሙ ትዊተር አሁን ኤክስ አካውንቱ ይፋ እንዳደረገው የግዛቴ አካል ናት ወደ ሚላት ሶማሊላንድ ሀርጌሳ እየበረረ የነበረ አውሮፕላን እንዳያርፍ…
Read More
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሱ-30 የጦር ጄቶች መታጠቁን ገለጸ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሱ-30 የጦር ጄቶች መታጠቁን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዘመናዊ የሆነውን የመጀመሪያ ዙር የsu-30 ተዋጊ ጀቶችንና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖች መረከቡን ተገለጸ። በርክክቡ ላይ የተገኙት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፤ በዓለማችን ላይ ተመራጭ የሆኑትን የsu-30 እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላን ባለቤት መሆናችን በሀገራችን ላይ ሊቃጡ የሚሞከሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የ5ኛ ትውልድ አካል የሆኑት ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖችና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አየር ሀይሉን የማዘመን አንዱ አካል መሆናቸውንም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት ሊከላከሉ የሚችሉ ዘመናዊ የውጊያ ትጥቆችን የመታጠቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኤታማዦር ሹሙ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ሀይል "በአፍሪካ በውጊያ አቅሙ፣ በጀግንነቱና በትጥቁ የነበረውን ዝና ዘመኑ በሚጠይቀው መልኩ ለማዘመን"…
Read More