DemekeMekonnen

አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣን ለቀቁ

አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣን ለቀቁ

የኢትዮጵያ ገዢ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣናቸው ለቀቁ፡፡  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሸኘታቸውን ፓርቲያቸው አስታውቋል። የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ " የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል አቶ ደመቀን በክብር ተሸኝተዋል " ሲል ገልጿል። አቶ ደመቀን መኮንንን በመተካት የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። አቶ ደመቀ ከፓርቲው አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች መሆኑ ተነግሯል። አቶ ደመቀ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና…
Read More